በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀድሞ የጊኒ አምባገነን መሪ ካማራ ፍርድ ቤት ቀረቡ


ፎቶ ፋይል፦ የቀድሞ የጊኒ ፕሬዚዳንት ሞሳ ዳዲስ ካማራ
ፎቶ ፋይል፦ የቀድሞ የጊኒ ፕሬዚዳንት ሞሳ ዳዲስ ካማራ

የቀድሞ የጊኒ አምባገነን ፕሬዚዳንት ሞሳ ዳዲስ ካማራና 10 የቀድሞ ወታደራዊ መንግሥት ባለሥልጣናት ለመጀመሪያ ጊዜ በአገሪቱ ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡

የቀድሞ ባለሥልጣናቱ ጳጉሜ 4 2001 ዓም በተካሄደው የተቃዋሚ ሰልፍና ከዚያ በኋላ ባሉት ጊዜያት ፈጽመውታል በተባለው ግፍና በደል ኮናክሪ በሚገኘው ፍርድቤ ት ቀርበው ምላሽ ይሰጣሉ ተብሏል፡፡

በወቅቱ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የተቃዋሚዎቹ ደጋፊዎች ፕሬዚዳንት ካማራን በመቃወም ምርጫ እንዲካሄድ በስቴዲዮም ውስጥ በተካሄደ ሰላማዊ ስብሰባ መጠየቃቸው ተዘግቧል፡፡

የጸጥታ ሰራተኞች ተቃዋሚዎችና በወቅቱ የነበረው ወታደራዊ መንግሥት ደጋፊዎች ከ150 በላይ ሰዎችን መግደላቸውና ቢያንስ 109 የሚደርሱ ሴቶችን መደፈራቸውን በተባበሩት መንግሥታት የተደገፈ የዓለም አቀፍ ኮሚሽን አመልክቷል፡፡

ባላሥልጣናቱ ለፍርድ እንዲቀርቡ የተጎጂዎቹ ቤተሰቦች ለዓመታት ሲጠይቁ መቆየታቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።

XS
SM
MD
LG