በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጊኒ በቶን የሚገመት ኮኬይን ከወደቧ ላይ ወረሰች


ፎቶ ፋይል፦ የቡልቢኔት ወደብ በኮናክሪ፣ ጊኒ
ፎቶ ፋይል፦ የቡልቢኔት ወደብ በኮናክሪ፣ ጊኒ

ጊኒ፣ በሴራሊዮን ሰንደቅ ዓላማ ከሚቀዝፍ መርከብ ላይ፣ 1ነጥብ 5 ቶን ኮኬይን ያዘች።

ካስማር በተባለ ወደቧ መልሕቁን ከጣለው እና በሴራሊዮን ባንዲራ ከሚቀዝፈው መርከብ ላይ፣ 1ነጥብ 5 ቶን የሚመዝን ኮኬይን የተባለ አደንዛዥ ቁስ መውረሷን ጊኒ አስታውቃለች፡፡

ሮይተርስ እንደዘገበው፣ እያንዳንዳቸው 25 ኪሎ ግራም ኮኬን የያዙ 60 ጥቅሎች፣ በመርከቡ ላይ መገኘታቸውን፣ የጊኒ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በመርከቡ ላይ የተገኙ ዐሥሩም ሠራተኞች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን፣ የጊኒ መንግሥት የዜና ማሠራጫ አመልክቷል፡፡

ሱስ አስያዥ መድኃኒትን በድብቅ የሚያስተላልፉ አካላት፣ የምዕራብ አፍሪካን ሀገራት፣ ከደቡብ አሜሪካ ወደ አውሮፓ ለማቀባበል፣ በብዛት እንደሚጠቀሙባቸው ሮይተርስ ጠቁሟል፡፡ ባለፈው ነሐሴም በጊኒ የባሕር ጠረፍ ላይ፣ ሦስት ቶን ኮኬይን እንደተያዘ፣ ዜናው አክሎ አውስቷል፡፡

XS
SM
MD
LG