በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቬኔዙዌላ ተቃዋሚ መሪ ሁዋን ጉዊይዶ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ


የቬኔዙዌላ ተቃዋሚ መሪ ሁዋን ጉዊይዶ
የቬኔዙዌላ ተቃዋሚ መሪ ሁዋን ጉዊይዶ

ዩናይትድ ስቴትስ በሽግግር ፕሬዚዳንትነት ዕውቅና የሰጠቻቸው የቬኔዙዌላ ተቃዋሚ መሪ ሁዋን ጉዊይዶ ዛሬ የሀገራቸው ውስጥ ሰልፍ እንዲወጣ ጥሪ አቀረቡ ። በላቲን አሜሪካ ወዳጅ ሃገሮች ያደረጉትን ጉብኝት አጠናቅቀው ወደሃገራቸው በሚመለሱበት ቀን ህዝቡ ሰልፍ እንዲወጣ ነው ያሳሰቡት ።

ሁዋን ጉዊይዶ ከኢኩዋዶር ፕሬዚዳንት ሌኒን ሞሬኖ ጋር ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ትናንት ዕሁድ ማታ ሳሊናስ ከምትባለው የጠረፍ ከተማ በኢኩዋዶር አየር ኃያል አውሮፕላን ተሳፍረው ወጥተዋል። የጉዞ መርኃ ግብራቸው አስቀድሞ ያልተገለጠው ተቃዋሚ መሪው ሁዋን ጉዌይዶ ዛሬ ወደካራካስ እንደሚመለሱ ቃል አቀባያቸው አስታውቋል። ስመለስ ያስሩኛል ብለው እንደነበር ይታወሳል።

የዩናይትድ ስቴትስ የብሄርዊ ፀጥታ አማካሪ ጆን ቦልተን ዛሬ ሰኞ በሰጡት ቃል ጉዌዶ ሲመለሱ ደኅንነታቸው ላይ አንዳች አደጋ ቢቃጣ ከዩናይትድ ስቴትስና ከዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ብርቱ አፀፋ ይከተላል ብለዋል።

በዩናይድ ስቴትስና በሌሎች ሃምሳ ሃገሮች በቬንዙዌላ የሽግግር መሪነት ዕውቅና ያገኙት ጉዌዶ የፓርላማው መሪ በዚያ ሥልጣናቸው ህገ መንግስቱን ጠቅሰው የፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማዱሮን አመራር ህገ ወጥ ሲሉ አውጀዋል።

ጉዊይዶ ባለፈው ሳምንት ከዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ እና ከሌሎች መሪዎች ጋር ኮሎምቢያ ዋና ከተማ ቦጎታ ላይ ተገናኝተው ተነግረው ከዚያ በኋላወደ ብራዚል እና ፓራጉዋይ ተጉዘዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG