በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ውይይት፡ የምዕራባውያን ወግና ልማዶችን ኢትዮጵያውያን የሚቀበሉበት መንገድ


ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን እና በምሕንድስና ሞያ ላይ የተሰማራውና የዩኒቨርስቲ መምሕሩ አቶ ረደኤት አባተ
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን እና በምሕንድስና ሞያ ላይ የተሰማራውና የዩኒቨርስቲ መምሕሩ አቶ ረደኤት አባተ

የአውሮፓውያን ባሕልና ባዕል የሆነው የሆነው ቫላንታይንስ ዴይ ወይም የፍቅር ቀንን ጨምሮ ሌሎች የምዕራባውያን ወግና ልማዶችን ኢትዮጵያውያን እንዳለ እየተቀበሉ ወይም ደግሞ አሳስተውና አጋነው እየወሰዱ ከባሕልና ማንነታችን ጋር እንዲቃረን ያደርጉታል ሲሉ በርካቶች ትችት ያቀርቡበታል። ከትችት አቅራቢዎች ውስጥ ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን እና በምህንድስና ሞያ ላይ የተሰማራውና የዩኒቨርስቲ መምሕሩ አቶ ረደኤት አባተን ጽዮን ግርማ አወያይታቸዋለች።

እንግዶቹን ጋብዘን ውይይቱን ለማድረግ መነሻ የሆነው ዋና ምክኒያት በየዓመቱ የሚከበረውና በዘንድሮው ዓመት ደግሞ ባለፈው ማክሰኞ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር የካቲት 14 በኢትዮጵያ በ7/2009 ዓ.ም የተከበረው የፍቅረኞች ቀን ነው። ይህ ባሕል በኢትዮጵያ በተለይ ደግሞ አዲስ አበባን ጨምሮ በአንዳንድ ከተሞች በወጣቶች ዘንድ መከበሩ እየተለመ የመጣ መምጣቱና የአከባበሩ አከራካሪነቱ እያመዘነ መምጣቱ ነው።

ይህን በተመለከተም የቪ.ኦ.ኤ አማረኛ የፌስቡክ ገጽ ላይ ተሳታፊዎች አስተያየት እንዲሰጡበት ጠይቀንም በርካታ ተሳታፊዎች አስተያየት ሰጥተዋል። አንዳንዶቹ “የፍቅር ቀን እስከሆነ ድረስ ከሌላ ሀገር ተቀብለን ብናከብረው ምንም ጉዳት የለውም” ሲሉ አብዛኞቹ አስተያየት ሰጪዎች ደግሞ አከባበሩ ከባህል ያፈነገጠ ነው ሲሉ ትችት ሰንዝረዋል።

ከኢትዮጵያ ባሕል ያፈነገጠና ከሌሎች የተኮረጀ ዘመናዊ መሰል ማፈንገጥ የሚከናወነው በቫላንታይንስ ቀን ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ድርጊቶች ጭምር ነው የሚል መከራከሪያም ያቀረቡ አልታጡም። ይህን ክርክር ይዘን በፌስቡክ ገፃቸው ላይ በጉዳዩ ላይ አስተያየት ሲሰጡ የነበሩ እንግዶችን ጋብዘናል። እንግዶቹ ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን እና በምህንድስና ሞያ ላይ የተሰማራውና የዩኒቨርስቲ መምሕሩ አቶ ረደኤት አባተ ናቸው።

ውይይት፡ የምዕራባውያን ወግና ልማዶችን ኢትዮጵያውያን የሚቀበሉበት መንገድ
please wait

No media source currently available

0:00 0:16:26 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG