በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግሪክ አምስት ድንበር ጠባቂዎችን ከሕገ ወጥ አስተላላፊዎች ጋራ በአባሪነት ጠርጥራ ያዘች


በግሪክ እና በቱርክ መካከል ያለ የድንበር አጥር፣
በግሪክ እና በቱርክ መካከል ያለ የድንበር አጥር፣

ግሪክ፣ ከጎረቤት ቱርክ ወደ ግዛቷ የሚገቡ ፍልሰተኞችን፣ ከሕገ ወጥ አዘዋዋሪዎች ጋራ በማበር ረድተዋል፤ በሚል የጠረጠረቻቸውን አምስት ልዩ የድንበር ጠባቂ ፖሊሶችን፣ ዛሬ በቁጥጥር ሥር ማዋሏን አስታወቀች።

ዛሬ የወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ አምስቱ ተጠርጣሪዎች፥ ከጥቅምት ወር መጨረሻ ጀምሮ፣ የኤቭሮስን ወንዝ የሚያቋርጡ ጀልባዎችን ተጠቅመው 100 ሰዎችን እንዲገቡ አመቻችተዋል፤ ተብሎ ይታመናል።

የኤቭሮስ ወንዝ፣ በአውሮፓ የተሻለ ሕይወት ለሚፈልጉ ሰዎች ወደ ግሪክ ለመግባት ቁልፍ ነጥብ እንደኾነም ተነግሯል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ድንበር ጠባቂ ፖሊሶች፣ በግሪክ ድንበር አቅራቢያ በምትገኝ ከተማ በተያዙበት ወቅት፣ ፖሊስ፥ 28ሺሕ ዶላር ጥሬ ገንዘብ እና 60 የሚጠጉ ሞባይል ስልኮችን አብሮ መያዙ ተገልጿል፡፡

ግሪክ፣ ፍልሰተኞች ወደ ግዛቷ እንዳይገቡ ለመከላከል፣ በድንበሯ ዙሪያ ግዙፍ አጥር የገነባች ሲኾን፣ የመከላከያ አጥሩን የበለጠ ለማራዘም ማቀዷም ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG