በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትልቁ የአፍሪካ ደን ልማት ፕሮጀክት ቸግሮታል


በታላቁ አረንጓዴ ግድግዳ ፕሮጀክት ከተተከሉ ዛፎች
በታላቁ አረንጓዴ ግድግዳ ፕሮጀክት ከተተከሉ ዛፎች

እኤአ እስከ 2030 ድረስ በአፍሪካ ሰሀራ በረሃ ከምዕራብ ሴኔጋል ጫፍ እስከ ጅቡቲ 8ሺ ኬሎሜትር የሚሸፍን ዛፍ በመትከል ለማልማት እኤአ በ2007፣ ታላቁ አረንጓዴ ግድግዳ በሚል ታስቦ የተጀመረው ፕሮጀክት እስካሁን ያሳካው 4 ከመቶ ብቻ መሆኑን ተነገረ፡፡

በሰሀራ በረሃ በታየው የአየር ንብረት ለውጥ፣ እየጨመረ በመጣው ሙቀትና፣ ወደ ደቡብ የሚከለበሰው የአሸዋ ማዕበልና በየጊዜው የሚጥለው ከባድ ዝናብ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን ማውደሙ ተነግሯል፡፡

እስከዛሬ ከተሳካው የ4 ከመቶ ሥራ ቀሪውን ለማሳካት ወደ 43 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ተመልክቷል፡፡

በሌላም በኩል እንደዚያ ያሉ ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ከመወጠን በአየካባቢው በየማህበረሰቡ በሚተከሉ ትናንሽ የችግኝ ፕሮጀከቶች ላይ ትኩረ እንዲደረግ መታቀዱም የገጠመውን የአየር ንብረት ቀውስ ለመቋቋም እንደሚያስችል በሰሞኑ የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ ተነስቷል፡፡

XS
SM
MD
LG