በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እየተሰጠ ነው


መቀሌ ከተማ
መቀሌ ከተማ

በትግራይ ክልል፣ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዛሬ ማክሰኞ የተጀመረ ሲኾን፣ ከ54ሺሕ በላይ ተማሪዎች ለፈተናው እንደሚቀመጡ፣ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል፡፡

በክልሉ በሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች ቅጽር በመሰጠት ላይ የሚገኘው ፈተናው፣ በሦስት ዙሮች እስከ ሐምሌ 12 ቀን 2016 ዓ.ም. እንደሚሰጥ ተመልክቷል፡፡

በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እየተሰጠ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:39 0:00

በክልሉ ለመጀመሪያ ጊዜም በበይነ መረብ የሚፈተኑ ተማሪዎችም እንዳሉ፣ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሓላፊ ዶክተር ኪሮስ ጉዕሽ ተናግረዋል፡፡

በሌላ ዜና፣ የትግራይ ክልል አመራሮች፣ ለፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት አፈጻጸም ግምገማ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልኡክ አምባሳደር ማይክ ሐመር በሚገኙበት ስብሰባ ላይ ለመካፈል ወደ ዐዲስ አበባ አምርተዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG