የሴት ልጅ ግርዛትና ያለ ዕድሜ ጋብቻን ለማስቆም አሁንም የተቀናጀ ስራ እንደሚያስፈልግ የገለፀው የኢትዮጵያ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒሰቴር፣ ከተባበሩት መንግሥታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) እና ከሌሎች አጋሮች ጋር በመተባበር ያዘጋጃቸውን ሰነዶች ዛሬ ይፋ አድርጓል ።
ጥር 29 ቀን 2017 ዓ/ም ይፋ የተደረጉት ብሔራዊ የዕቅድ ሰነዶች ችግሩን እ.አ. አ. እሰከ 2030 ለመፍታት ያስችላሉ የተባሉ ናቸው።
የተፈጥሮ አደጋዎች እና ግጭቶች ታዳጊ ሴቶችን ለተጠቀሱት ችግሮች እያጋለጡ መሆኑን የተናገሩት፣ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ምኒሰትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ "ትልቁ ነገር ሰላም ላይ መስራት ነው" ብለዋል።
ድርጊቶቹ ሰብዓዊ ቀውስ በሌለበት ሁኔታ ውስጥም እየተፈጸሙ ናቸው ያሉት በኢትዮጵያ የዩኒሴፍ ተጠባባቂ ተወካይ ማሪኮ ካጎሺማ፣ ሰነዶቹ የግንዛቤ ለውጥ ለማምጣት እንደሚያግዙ ጠቅሰዋል።
መድረክ / ፎረም