በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት መግለጫ እና የህወሓት ምላሽ


የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት መግለጫ እና የህወሓት ምላሽ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:08 0:00

የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት መግለጫ እና የህወሓት ምላሽ

በፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት መሠረት፣ ጦርነትን በፖለቲካዊ መፍትሔ በመቋጨት የመልሶ ማቋቋም እና የመልሶ ግንባታ ሥራዎች እየተከናወኑ ቢኾኑም፣ የህወሓት ታጣቂዎች ትጥቅ መፍታት ከቀሪ ሥራዎች ውስጥ እንደኾነ የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ገለጸ፡፡

ምክር ቤቱ፣ ትላንት ረቡዕ ባወጣው መግለጫ፣ በአንድ ሀገር ከመንግሥት የመከላከያ ኀይል ውጭ ሌላ የታጠቀ ኀይል እንዲኖር ሕገ መንግሥቱ እንደማይፈቅድ ጠቅሶ፣ “በስምምነቱ መሠረት የህወሓት ታጣቂዎች ትጥቅ መፍታት አለባቸው፤” ብሏል፡፡

በጦርነቱ የተፈናቀሉትን ለመመለስና ለማቋቋም የተጀመሩ ሥራዎች እልባት ማግኘት እንዳለባቸው በመግለጫው ያስገነዘበው ምክር ቤቱ፣ “ካለፈ ስሕተት አለመማር የመጀመሪያውን ስሕተት ከመሥራት የባሰ ነው፤ ካለፈው ስሕተታቸው ሳይማሩ ዛሬም ተመሳሳይ ችግር ለመፍጠር የሚከጅሉትን ኹላችንም ተባብረን አደብ ማስገዛት ይኖርብናል፤” በማለት አሳስቧል፡፡

በጉዳዩ ላይ ለአሜሪካ ድምፅ ምላሽ የሰጡት በህወሓት ጽሕፈት ቤት የፕሮፓጋንዳ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኢያሱ ተስፋይ፣ ፓርቲያቸው ሰላም ስትራቴጂያዊ ምርጫው መኾኑን ተናግረዋል፡፡

በስምምነቱ እንደሰፈረው፣ የፌደራሉ መንግሥት ከመከላከያ ሠራዊት ውጭ ያሉ ታጣቂዎች ከክልሉ ማስወጣት እንዳለበት ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG