በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ


የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

የህወሓት ተግባር የፌደራል መንግሥቱን ትዕግስት እየፈተነ እና ከመከላከል ወደ ማጥቃት እንዲገባ እየገፋው ነው ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት አስጠነቀቀ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አካፋን አካፋ ብሎ ለመጥራት ጊዜው አሁን ነው ብሏል።

ህወሓት የጥይት ጋሻ አድርጎ ለተጠቀማቸው በሽሕዎች የሚቆጠሩ ትዳጊ ሕጻናት ሞት ተጠያቂ መሆን እንዳለበትም አመልክቷል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ላለው ሁኔታ ዘለቄታዊ መፍትሄ ለማምጣት ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም በማለትም አክሏል መግለጫው።

"ነገር ግን መንግሥት ሕወሓት ለቀጠለው ግጭቱን ወደ አጎራባች ክልሎች የማስፋትና አገሪቱን የማተራመስ እንቅስቃሴ ምላሽ ለመስጠት እየተገደደ ነው" ብሏል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር::

የኢትዮጵያ መንግሥት ሲተገብረው የቆየው የተናጥል የተኩስ አቁሙ አዋጅ መቼ እንደሚነሳ ወይም እየተነሳ ስለመሆኑ ግን መግለጫው አላብራራም።

በቅርቡ ለቢቢሲ ዓለም አቀፍ አገልግሎት መግለጫ የሰጡት የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ሚኒስትር ዛድግ አብራሃ የመንግሥት ትዕግስት በቅርቡ ሊያልቅ ይችላል የሚል እንድምታ ያለው አስተያየት ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ትዕግስት የሚያልቀው መቸ ነው? የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት የፕሬስ ክፍል ሃላፊ ቢለ ለኔ ስዩም "ያ የሚወሰነው በብሔራዊ የደህንነት ምክር ቤት ነው" ብለዋል።

ኤኤፍፒ የጠቀሳቸው የሕወሓት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ታጣቂዎቻቸው ከአጎራባች ክልሎች እንደማይወጡ ተናግረዋል።

ይህ ደግሞ ተጥሏል ያሉት የሰዓብአዊ እርዳታ ተደራሽነት ገደብ እስኪነሳ እና "ከበባ" ሲሉ የገለጹት ሁኔታ እስኪቀየር እንደሚቀጥል ነው የጠቆሙት።

XS
SM
MD
LG