የአይሮፕላን ጣቢያው ቀድሞም የነበረና ከሃምሣ ዓመታት ዕድሜ በላይ ያስቆጠረ ቢሆንም ድንገት ከተዘጋ በኋላ የአካባቢው ነዋሪ የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዳያገኝ መደረጉን፣ ታሪካዊና ባሕላዊ እሴቶቹ እንደቀድሞው እንዳይወጡ እንቅፋት መሆኑን፣ ቀድሞ በስፋት ይታይ የነበረው ከውጭ የሚሄዱ ሃገር ጎብኝዎች ፍሰት መቋረጡን ሪፖርተራችን ናኮር መልካ ያነጋገራቸው ነዋሪዎችና አባ ገዳ ተናግረዋል።
በሰልፉ ምክንያት ተዘግቶ የነበረው ወደ አዲስ አበባና ጋምቤላ የሚወስደው መንገድ መከፈቱን የአሌ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ነበራ ቡሊ ተናግረዋል።
የሰልፉን አስተባባሪዎች፣ ተሣታፊዎችን፣ የወረዳና የዞን አስተዳዳሪዎችን ያነጋገረው ናኮር ዝርዝር ዘገባውን በነገው ምሽት ይዞ ይመለሳል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ