ዋሺንግተን ዲሲ —
እስያ ውስጥ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ የጉግል ሰራተኞች ዛሬ ለአጭር ጊዜ ከሥራ የመውጣት አድማ መተዋል። የጎግል ኩባንያ የፆታዊ ወከባንና የሥራ ቦታ ባህሉን አያያዝ በሚመልከት በዓለም ደረጃ የሚካሂደው ተቃውሞ አካል ነው።
አብዛኞቹ ሴቶች የሆኑ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሌሎች ሰራተኞች ደግሞ ዛሬ በዓለም ዙርያ ካሉት የጎግል ኩባንያዎች ከሥራ የመውጣት አድማ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ግዙፍ የኢንተርኔት ኩባንያ የሆነው ጎግል ሰራተኞችን በማዋከብ ተግባር የተከሰሱ ወንዶች ባለሥልጣኖችን ስለፈፀሙት በደል ሳያሳውቅ በሚልዮኖች የሚቆጠር ዶላር ከፍሎ ሸኛቸው የሚል ወሬ ባለፈው ሳምንት በኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ላይ ከወጣ በኋላ ከሥራ የመውጣቱ አድማ እንደተባባሰ ተዘግቧል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ