በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ህወሓት በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ውድመት ማደረሱ ተገለጸ


ፎቶ ፋይል፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
ፎቶ ፋይል፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

ህወሓት በተቆጣጠራቸው የሰሜን ወሎና የጎንደር አካባቢዎች ሆን ብሎ የህዝቡን የኢኮኖሚ መሰረቶች ማውደሙን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ አሸባሪው ያለው የህወሓት ወታደሮች እና ተባባሪዎቻቸው የደረሱ ሰብሎችን እየዘረፉ ስለመሆናቸው በአካባቢው የሚገኙ አርሶ አደሮች ሪፖርት ማድረጋቸውን ጠቁሟል፡፡

ሚኒስቴሩ በመግለጫው፣ ህወሓት በግለሰቦች ላይ አድርሷል ካላቸው ጉዳቶች ባለፈ በብዙ አካባቢዎች የማህበረሰቡ መገልገያ የሆኑ ተቋማትን ማውደሙንም ጠቅሶ፣ እነዚህ ድርጊቶች በአማራ እና በትግራይ ህዝብ መካከል ጥላቻን እና ቂምን ከማባባስ ባለፈ፣ ለትግራይ ህዝብ የሚፈይዱት ነገር እንደሌለም ነው የገለጸው፡፡

ለመግለጫው ቀጥተኛ ምላሽ ያልሰጠው ህወሓት በበኩሉ፣ ከዚህ ቀደም በሰጣቸው መግለጫዎች መሰል ውንጀላዎችን ሲያጣጥል ቆይቷል፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ህወሓት በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ውድመት ማደረሱ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:03 0:00


XS
SM
MD
LG