በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"በጎንደር ታሪካዊ ቅርሶችና ቱሪዝም አደጋ ላይ ናቸው"


በዓለም አቀፍ የቅርስ ሀብትነታቸው በዩኔስኮ የተመዘገቡት የጎንደር ቅርሶች የእድሳት ችግር፣ የጎብኝዎችና የገቢ እጥረት የገጠማቸው መሆኑን የጎንደር ዐለም አቀፍ ቅርስ አስተዳደር አስተዳዳሪ አቶ ጌታሁን ስዩም ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል፡፡

በተለይም በአለፉት ሶስት ዓመታት በአገሪቱ በነበሩ ሁኔታዎችና በተከሰተው የኮቪድ 19 ወረርሽን ሳቢያ ቅርሶቹ ብርቱ ችግር ላይ መሆናቸውን የገለጹት አቶ ጌታሁን የአጼ ፋሲል ቤተመንግስት ጊቢና መዋኛውን ጨምሮ በጎንደር ከተማ ውስጥ የሚገኙት ጥንታዊ ቤተመንግስቶቹና ታላላቅ ቅርሶቹ አስቸኳይ ትኩረት የሚሹ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

እሳቸው እንደሚሉት "በጎንደር ከተማ የቱሪዝም እንቅስቃሴ ቆሟል" ማለት ይቻላል፡፡

በዓለም አቀፍ የቅርስ ሀብትነታቸው በዩኔስኮ ከተመዘገቡት 9ኙ የጎንደር ቅርሶች የሰባቱ ቅርሶች አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ጌታሁን እንደሚሉት በዓመት ከቱሪዝም ይገኝ የነበረው ከ7 እስከ 10 ሚሊዮን አማካይ ገቢ አሁን ወደ 600 ሺ ወርዷል፡፡ የጎብኝዎችም ቁጥር ወደ ጥቂት መቶዎች አሽቆልቁሏል፡፡

ይህም ሆኖ ደግሞ የመሰነጣጠቅ ችግር እየደረሰባቸው ያሉት ቅርሶቹም ደህንነት አደጋ ላይ ይገኛል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

"በጎንደር ታሪካዊ ቅርሶችና ቱሪዝም አደጋ ላይ ናቸው"
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:38 0:00

XS
SM
MD
LG