በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጎንደር የዛሬ ውሎ


ፎቶ ፋይል፦ ጎንደር ከተማ
ፎቶ ፋይል፦ ጎንደር ከተማ

በቅርቡ የሰው ህይወት የጠፋበት ግጭት የተካሄደባት ጎንደር ከተማ ዛሬ የንግድ ተቋማት መከፈታቸው እና የትራንስፖርት አገልግሎት መጀመሩን የከተማዋ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የከተማ አስተዳደር ቃል አቀባይ አቶ አበበ ላቀው ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል በከተማዋ እና በአካባቢዋ በፋኖ ቡድን ታጣቂዎችና በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች መካከል በተከሰተው ግጭት ምክንያት “በንፁሃን ዜጎች ላይ ስለደረሰው ጉዳት ምርመራው ሲጠናቀቅ እናሳውቃለን” ብለዋል፡፡

በሰሞኑ ግጭት ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች መሞታቸውን ነዋሪዎች ትናንት ሰኞ ለአሜሪካ ድምፅ መናገራቸው ይታወሳል፡፡

መጪውን የጥምቀት በዓል ለማክበር የሚያስችል የፀጥታ ሁኔታ አለ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተጠናቅቋል ጎብኝዎች ያለ ምንም ስጋት በዓሉን መጥተው መታደም ይችላሉ”

የከተማዋ አስተዳደር ቃል አቀባዩ አክለውም “መጪውን የጥምቀት በዓል ለማክበር የሚያስችል የፀጥታ ሁኔታ አለ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተጠናቅቋል ጎብኝዎች ያለ ምንም ስጋት በዓሉን መጥተው መታደም ይችላሉ” ብለዋል፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ግን በከተማው አልፎ አልፎ እየተከሰተ ያለው ግጭት የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ጎብኝዎች ታድመው በዓሉ በደመቀ ሁኔታ እንዳይከበር እንቅፋት እየሆነ ነው” ብለዋል፡፡

የዚህን ዘገባ ዝርዝር ከተያያዘው ፋይል ያድምጡ፡፡

ጎንደር ከተማ.mp3
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:28 0:00

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG