በኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥትና በህወሓት መካከል ድርድር ሊደረግ መሆኑን የሚጠቁሙ ሪፖርቶች እየወጡ ነው። ታንዛኒያ ውስጥ ሊካሄድ ታቅዷል” ስለተባለው ድርድር ሁለቱም ወገኖች ግን ማረጋገጫ አልሰጡም። በሌላ በኩል ደግሞ የአማራና የትግራይ ክልሎች መሪዎች በተለይ በአወዛጋቢው የወልቃይት ጉዳይ ላይ ሰፊ ልዩነት አንፀባርቀዋል።
“’ወልቃይት’ ወይም ‘ምዕራብ ትግራይ’ ለድርድር አይቀርብም” ብለዋል የሁለቱም ባለሥልጣናት።