በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

76ተኛው ጎልደን ግሎብ የሽልማት ሥነ ሥርዓት


76ተኛው ጎልደን ግሎብ ሽልማት
76ተኛው ጎልደን ግሎብ ሽልማት

".. ሕልማችንን ዕውን ለማድረግ በምናደርገው ትግል .. አሳካዋለሁ ብለን መነሳት መቻል፣ በግል ሕይወታችን እርካታ መጎናጸፍ አለብን።..” 'The Wife' በተሰኘው ፊልም ላይ ዋናዋን ገጸ ባሕሪ ጆአን ካስልማን’ን ሆና ባሳየችው ድንቅ አጨዋወት በዘንድሮው ጎልደን ግሎብ ከሴት ተዋናዮች የዓመቷ ምርጥ ተዋናይ ግሌን ክሎዝ።

ዓመታዊው ጎልደን ግሎብ የሽልማት ሥነ ሥርዓት በሎሳንጀለሷ የቤቨርሊ ሂል ከተማ በቅርቡ ተካሂዷል። እንደ ወትሮው ሁሉ ዘንድሮም ባሳለፍነው የአውሮፓውያኑ 2018 የዓመቱ ምርጥ ፊልሞችና የቴቭዥን ድራማዎች የምርጦቹን ምርጦች መርጧል።

ከፍተኛ አድናቆት ባተረፈው 'Crazy Rich Asians' በተሰኘው ፊልም የተጫወተችው፣ ከኮሪያውያን ወላጆቿ በካናዳ የተወለደችው ሳንድራ ኦህ ከኤንዲ ሳምብርግ ጋር መድረኩን እንድትመራ ስትታጭ የፍርሃት ስሜት አድሮባት እንደነበር ነገር ግን በመጨረሻው “የለውጥ ኃይል” ያለችውን ታዳሚ ለማየት “እሺ ብያለሁ” ስትል መድረኩን በጋራ የመምራቱን ኃላፊነት መረከቧን ተናግራለች።

'BlacKkKlansman' .. 'If Beale Street Could Talk' .. 'Star Is Born' እና 'Black Panther' ዕጩ ሆነው በቀረቡበት ድራማ ዘርፍ ቦሄሚያን ራፕሲዲ በዓመቱ ምርጥ ፊልምነት ሲመረጥ ራም ማሊክ በዘርፉ የዓመቱን ምርጥ ተዋናይ ሽልማት ተቀብሏል።

ታላቁን የድል ጽዋ ለመጎንጨት ባይብቁም በዘርፉ በምርጥ ፊልምነት ከታጩት ከአምስቱ ሦሥቱ ጥቁር አሜሪካውያን ተዋናዮች የተጫወቱባቸው ግሩም ፊልሞች ናቸው።

ሽልማቱን ስትቀበል ያሰማችው መሳጭ ንግግር - በፊልሙ የተጫወተቻት ገጸ ባሕሪ ለባሏ ሥኬት ራሷን የሰጠችበትን ስሜት ዳግም ለታዳሚው ቅርብ አድርጋለች።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

76ተኛው ጎልደን ግሎብ የሽልማት ሥነ ሥርዓት
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:19 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG