በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ወርቅ አገኘች


ካቲ ናጊዮት በምርኩዝ ዝላይ ለዩናይትድ ስቴትስ ወርቅ አስገኝታለች
ካቲ ናጊዮት በምርኩዝ ዝላይ ለዩናይትድ ስቴትስ ወርቅ አስገኝታለች

ዩናይትድ ስቴትስ አመሻሹን የሜዳሊያ ብዛቷን ከፍ ያደረጉ ድሎችን አስመዝግባለች። ካቲ ናጊዮት በምርኩዝ ዝላይ ለዩናይትድ ስቴትስ ወርቅ አስገኝታለች። 4.9 ሜትር ከፍታ በመዝለል ፣ አንጀሊካ ሲዶሮቫ ከሩሲያ፣ ሃሊ ብራድሾ ከእንግሊዝ የብር እና ነሃስ ሜዳሊያዎችን ወስደዋል።

በአሎሎ ውርወራ በራዬን ክረውሰር አማካይነት ሌላ ወርቅ አክላለች። ራዬን የተዘጋጀውን አሎሎ 23 .3 በማሽቀንጠር የኦሎምፒክ ክብረወሰንን ሰብሯል። ሌላው የሀገሩ ልጅ ጆ ኮቫክስ የብር ፣የኒው ዚላኑ ቶም ዋልሽ የነሃስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆነዋል። አመሻሹን በነበረ የሴቶች እግር ኳስ ውድድር ዮናይትድ ስቴትስ አውስትራሊያን 4-3 በመርታት የነሃስ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆናለች።

***

በአጠቃላይ ሜዳሊያዎች ብዛት በሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ቻይና የእንግሊዝ ለንደን ኤምባሲ ቢቢሲ የተሰኘው የሀገሪቱ የዜና አውታር የታይዋን “ቻይኒዝ ታይፔ የኦሎምፒክ ቡድንን አስመልክቶ ያቀረበውን ዘገባ በእጅጉ ተቃውሟል። ኤምባሲው ተቃውሞውን በገለጸበት ደብዳቤ ላይ “በዓለም ላይ ያለችው ቻይና አንድ ብቻ ናት፣ ታይዋን ጥርጥር የሌለው የቻይና ግዛት ናት። የህዝባዊ ቻይና ሪፐብሊክ መንግሥትም ብቸኛው ህጋዊ መላ ቻይናን የሚወክል መንግሥት ነው” ብሏል። ዘገባው የሮይተርስ ነው።

ይህ በእንዲህ እያለ ቻይና አመሸሹን ተጨማሪ ሜዳሊያዎችን ሰብስባለች። በከፍታ ላይ በመዝለል በአስደናቂ ሁኔታ ተገለባብጦ ውሃ ውስጥ መጥለቅ ዘርፍ የ14 ዓመቷ ኳን ሆንግ ቻን ድል አድርጋለች። ሌላዋ የቻይና ውድድር ቺን የክዚ የብር ሜዳሊያን ስታሸንፍ፣ መሊሳ ዉ ከአውስትራሊያ የነሃስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆናለች። ከዚህ በተጨማሪ የቻይና ብሄራዊ ቡድን የጃፓን አቻውን በጠረጴዛ ቴኒስ ፍልሚያ በመርታት ወርቁን ወስዷል።

***

ኢትዮጵያ በወንዶች 1500 ሩጫ ውድድር ማጣሪያ ላይ ያሳተፈቻቸው አትሌቶች ማጣሪያውን ማለፍ ሳይችሉ ቢቀሩም ፍሬወይኒ ገብረግዘአብሄር ግን በሴቶች ዘርፍለፍጻሜው አልፋለች፣ በነገው ዕለት የፍጻሜ ውድደሯን ታደርጋለች።

በሜዳሊያ ብዛት የሚመሩትን ሀገራት ለመስታወስ ያህል ዩናይትድ ስቴትስ በ91 ሜዳሊያ አንደኛ ደረጃን ስትይዝ፣ ቻይና በ74 የሩሲያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ደግሞ በ58 ሜዳሊያዎች በ3ተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

XS
SM
MD
LG