በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በምዕራብ ጉጂ እና በጌዴዖ ህዝቦች መካከል የዕርቅ ሥነ ስርዓት ተካሄደ


በምዕራብ ጉጂ እና በጌዴዖ ህዝቦች መካከል የዕርቅ ሥነ ስርዓት ተካሄደ
በምዕራብ ጉጂ እና በጌዴዖ ህዝቦች መካከል የዕርቅ ሥነ ስርዓት ተካሄደ

በምዕራብ ጉጂ እና በጌዴዖ ህዝቦች መካከል በዛሬው ዕለት የዕርቅ ሥነ ስርዓት ተካሂዷል።

በዕርቅ ሥነ ስርዓቱ ላይም የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳና የደቡብ ክልል ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የሁለቱ ክልሎች የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል ሲል ፋና ብሮድካስቲንግ ዘግቧል።

የጉጂ እና የጌዴዖ አባ ገዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የአካባቢው ነዋሪዎች በዛሬው ዕለት በተካሄደው የዕርቅ ሥነ ስርዓት ላይ ታድመዋል።

ዕርቁን ተከትሎም በአካባቢው ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ከሁለቱም አካባቢዎች ማለትም ከኦሮሚያ ክልል ምእራብ ጉጂ ዞን እና ከደቡብ ክልል ጌዴዖ ዞን የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀድሞ መኖሪያቸው መልሶ የማቋቋም ሥራ በይፋ መጀመሩን የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቀዋል ይላል ፋና ብሮድካስቲንግ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG