ባለፈው ዓመት ሐምሌ አጋማሽ ላይ፣ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ጎዚዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የተፈናቀሉ 627 አባወራዎች፣ በነቀዝ ከተበላሸ በቆሎ በቀር በቂ ሰብአዊ ድጋፍ እንዳልቀረበላቸው ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።
ከተለያዩ ኢትዮጵያውያን በተሰበሰበው የገንዘብ ድጋፍ "በአጭር ጊዜ ውስጥ ቤት ይሠራላችኋል፤" ተብለው እንደነበር ያወሱት ተፈናቃዮቹ፣ ኾኖም የተባለው ቤት እንዳልተሠራላቸውና የተሰበሰበው ገንዘብም የት እንደደረሰ እንደማያውቁ ጠቁመዋል።
የአሜሪካ ድምፅ ለዞኑ አስተዳዳር እና ለክልሉ ባለሥልጣናት ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ቢያደርግም አያነሡም።
ኾኖም፣ የጎፋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ዳግማዊ አየለ ለደቡብ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል፣ 110 ቤቶች ተገንብተው ለተፈናቃዮች ማስረከባቸውን አስታውቀዋል።
የክልሉ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር አቶ ጋንታ ጋምአ በበኩላቸው፣ ድጋፍ እየቀረበ ነው፤ ብለዋል።
የሐዋሳው ዘጋቢያችን ዮናታን ዘብዴዎስ ተጨማሪ ዘገባ አለው። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም