ከ133 አገሮች የተሰባሰቡ የሕዝብ አስተያታየት ግምገማዎች ያካተተው እና በዛሬው ዕለት ይፋ የተደረገው የአገራት የአመራር ብቃት የተጠየቀበት አንድ ጥናት፣ ጀርመን በዓለም አቀፍ ደረጃ ቀዳሚውን እርከን መቆናጠጧን አመላከተ።
ያለፈው የአውሮፓውያኑ 2023 የአገራቱ የአመራር ብቃት በተመዘነበት በዚህ ግምገማ ጀርመን በ46 በመቶ ነጥብ ስትመራ ዩናይትድ ስቴትስ በ41 በመቶ በቅርብ ርቀት የሁለተኛውን ደረጃ ይዛለች።
በአውሮፓ ግዙፍ ኢኮኖሚ ያላት ጀርመን በአህጉር ደረጃ 60 ነጥብ በማስመዝገብ የአመራር ብቃት ማሳያ ሆናለች። ይህም ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ሲነጻጸር በእጥፍ ብልጫ የታየበት አሃዝ ነው።
በታሪክ የቀዳሚውን እርከን በመያዝ ትታወቅ የበረችው ዩናይትድ ስቴትስ በአንዳንድ የአፍሪካ አገሮች እና፣ ከዓለም በሕዝቧ ብዛት ሁለተኛ በሆነችው ህንድ የአመራር ብቃቷ ተቀባይነት በመጠኑ አነስ ብሎ ተገኝቷል።
በጋዛ ያለው ግጭት በአንዳንድ አገሮች የዩናይትድ ስቴትስ የአመራር ብቃት ግምገማ ላይ ተጽዕኖ ሳያሳድር እንዳልቀረ ተመልክቷል። የጥናት ቡድኑ አክሎ እንደጠቆመውም የጋዛው ግጭት ከጀመረ በኋላ ጥናት በተደረገባቸው አንዳንድ አገሮች መጠነኛ ማሽቆልቆል ታይቷል።
የሕዝብ አስተያየት ግምገማው 88 በመቶ ተቀባይነት የማጣት ነጥብ ያስቆጠረችውን ሩስያን በአመራር ብቃቷ የመጨረሻዋ አገር አድርጓታል።
መድረክ / ፎረም