በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 እና የዓለም ኢኮኖሚ


ፎቶ ፋይል፦ የኮቪድ ክትባት
ፎቶ ፋይል፦ የኮቪድ ክትባት

የዓለም ሃገሮች በኮቪድ-19 ሳቢያ ከደረሰባቸው ጉዳት ቀስ በቀስ እያገገሙ በመሆናቸው በዚህ የአውሮፓ 2021 የዓለም አኮኖሚ ጠቀም ያለ ዕድገት ያሳያል ሲል የአውሮፓ ትብብር እና ልማት ድርጅት ተነበየ።

ጽህፈት ቤቱ ፓሪስ የሆነው ድርጅቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የዓለም ኢኮኖሚ ቀደም ብሎ በታህሳስ ወር ላይ እንደተነበየው በ4 ነጥብ 2 ከመቶ ሳይሆን በ5 ነጥብ 6 ከመቶ እንደሚያድግ ገልጿል።

ለዚህ የተሻሻለ ትንበያው መሰረት ያደረገው በዓለም ዙሪያ የኮቪድ-19 ክትባት እየተሰጠ መሆኑን እና በዩናይትድ ስቴትስ የቀረበውን የ1 ነጥብ 9 ትሪሊዮን ዶላር የኮቪድ-19 ማገገሚያ ድጋፍ ወጭ መሆኑን አስታውቋል።

የዩናይትድ ስቴትሱ የየኮቪድ-19 ማገገሚያ ዕቅድ የዓለም ኢኮኖሚን በአንድ ከመቶ ከፍ ያደርገዋል ሲል ጠቁሟል።

ሆኖም የኮቪድ ክትባት ሂደት የተፋጠነ አለመሆኑ እና አዳዲስ የቫይረስ ዝርያዎች ብቅ ማለታቸው በኢኮኖሚዎች ማንሰራራት ላይ ከበድ ያለ አደጋ መደቀናቸው እንደማይቀር ድርጅቱ ሳያስጠነቅቅ አላለፈም።

XS
SM
MD
LG