በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ብዛት በዓለም ከፍተኛውን ቁጥር አስመዘገበ


ከሱዳን የፈለሱ ሰዎች ቻድ መጠልያ ጣቢያ ውስጥ
ከሱዳን የፈለሱ ሰዎች ቻድ መጠልያ ጣቢያ ውስጥ

ባለፈው ዓመት መጨረሻ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ቁጥር፣ 71ነጥብ1 ሚሊዮን በመድረስ፣ ከፍተኛውን ቁጥር ማስመዝገቡን፣ የአገር ውስጥ ተፈናቃይነትን የሚከታተለው ማዕከል፣ ዛሬ ኀሙስ ያወጣው ዘገባ አመለከተ፡፡

የተፈናቃዮቹ ቁጥር፣ እአአ በ2021 ከነበረበት፣ ባለፈው 2022፣ በ20 ከመቶ መጨመሩንም ዘገባው አመልክቷል፡፡

ባለፈው ዓመት መጠናቀቂያ ላይ ለታየው የዐዲስ ተፈናቃዮቹ ቁጥር መጨመር ምክንያት ከኾኑት መካከል፣ ማዕከሉ በዩክሬን ጦርነት ተፈናቅለዋል ያላቸውን 17 ሚሊዮን ሰዎችንና በፓኪስታን በደረሰው ትልቁ የጎርፍ አደጋ የተፈናቀሉትን ስምንት ሚሊዮን ሰዎች ጠቅሷል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ ግጭቶች እና ጥቃቶች፣ ባለፈው የ2022 ዓመት መጨረሻ፣ ለ62ነጥብ5 ሚሊዮን የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች መንሥኤ መኾኑንም ዘገባው ጠቁሟል፡፡

ከዓለም አቀፍ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች መካከል፣ ወደ ሦስት እጅ ያህል የሚጠጋውን ቁጥር ያስመዘገቡት 10 አገሮች፥ ሶሪያ፣ አፍጋኒስታን፣ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ፣ ዩክሬን፣ ኮሎምቢያ፣ ኢትዮጵያ፣ የመን፣ ናይጄሪያ፣ ሶማልያ እና ሱዳን መኾናቸውን ዘገባው አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG