በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 በዓለም


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ዓለማቀፍ የኮቪድ-19 ወረርሽኙ ይዞታ የሚከታተለው የዩናይትድ ስቴትሱ የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የመረጃ ማዕከል ዛሬ ዐርብ ያወጣው አሃዝ፤ በዓለም ዙሪያ የኮሮናቫይረስ ተያዦች ቁጥር 105,006,686፤ በበሽታው ምክንያት ለህልፈት የተዳረጉት ሰዎች ቁጥር ደግሞ 2,287,129 ገብቷል።

ከሃያ ስድስት ሚሊዮን በላይ የኮሮናቫይረስ ተጋላጭ የያዘችው ዩናይትድ ስቴትስ ከዓለም ቀዳሚውን ስፍራ እንደያዘች ስትሆን ህንድ አስር ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ብራዚል ዘጠኝ ነጥብ ሶስት ሚሊዮን ይዘው ይከተላሉ።

በዩናይትድ ስቴትስ ከነገ ወዲያ ዕሁድ በየዓመቱ የሚካሄደው ሱፐርቦል በመባል የሚታወቀው የአሜሪካ የእግር ኳስ የዋንጫ ግጥሚያ ይካሄዳል። በየዓመቱ በርካታ ሰዎች በትላልቅ መኖሪያ ቤቶች በመጠጥ ቤቶች እና ምግብ ቤቶች ዝግጅት በማሰናዳት ታድመው ይከታተላሉ። የጤና ባለሥልጣናት ታዲያ ህዝቡ ዘንድሮ በሱፐርቦል ግጥሚያ ዝግጅት ተሰብስቦ ለኮሮናቫይረስ አብዝቶ የሚዛመትበት ሁኔታ ከመፍጠር እንዲቆጠብ የጤና ባለስልጣናት እያሳሰቡ ናቸው፤ የስፖርቱ አፍቃሪ የዘንድሮውን ግጥሚያ አብሮት ከሚኖር ሰው ጋር ብቻ ተወስኖ እንዲከታተል የጤና ባለሥልጣናቱ መክረዋል።

XS
SM
MD
LG