በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በውጊያ ለተጠመደው የሱዳን ህዝብ ዐለም አቀፉ ማኅበረሰብ ተጨማሪ እርዳታ እንዲሰጥ ተጠየቀ


የዐለም አቀፍ ቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ ማኅበራት ዋና ጸሐፊ ጃጋን ቻፓጌን
የዐለም አቀፍ ቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ ማኅበራት ዋና ጸሐፊ ጃጋን ቻፓጌን

የዐለም አቀፍ ቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ ማኅበራት ዋና ጸሐፊ ጃጋን ቻፓጌን ትናንት ዕሁድ ለአሶሲየትድ ፕሬስ በሰጡት ቃል የዕርዳታ ድርጅቶች ሱዳን ውስጥ በሁለቱ ጄኔራሎች መካከል በሚካሄደው ጦርነት የተጠመደውን ሕዝብ ለመርዳት ከጠየቁት 45 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ እስካሁን ያገኙት 7 ከመቶውን ብቻ መሆኑን ገልጸዋል።

ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ባለፈው ዓመት ከሩሲያ ወረራ ሸሽተው ለተሰደዱ ዩክሬናውያን ያሰየውን ድጋፍ ለሱዳን ድጋፍ ለሱዳን ህዝብም እንዲያሳይ የዐለም ቀይ መስቀል ቀይ ጨረቃ ፌዴሬሽን ባለስልጣኑ ተማጽነዋል።

"ለዩክሬን የተደረገው ዓለም አቀፍ ድጋፍ ድጋፍ ጥሩ ምሳሌ ነው' ያሉት የአይሲአርሲ ዋና ጸሐፊ "አሁን ደግሞ ለሱዳን ተመሳሳይ ድጋፍ ማሳየት ይገባናል" ብለዋል።

የረድኤት ድርጅቶች ሱዳን ውስጥ በጦርነቱ ለተጠመደው ሕዝብ ከተጠየቀው 45 ሚሊዮን ዶላር በተጨማሪ አገራቸውን ጥለው ወደ አጎራባች ሀገሮች ለተሰደዱት መርጃ የሚሆን የተጨማሪ የ35 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍም ተማጽነዋል።

የዐለም ቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ ማሕበራት ፌዴሬሽኑ ዋና ጸሐፊ ተጨማሪ ዕርዳታ ተማጽኖውን ያቀረቡት ሱዳንን እና ግብጽን

ወደሚያዋስነው ድንበር አካባቢ ተጉዘው ከሱዳናውያን ስደተኞች እና ከድንበር ጥበቃ ባለሥልጣናት ጋር ከተገናኙ በኋላ መሆኑን አሶስየትድ ፕሬስ ጨምሮ ዘግቧል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG