በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የ‘ሎሚ’ አሣታሚ ተፈረደበት


ግዛው ታየ ክሡ ድሮም እኛን ለመዝጋት ነበር ብሏል፡፡

የ‘ሎሚ’ አሣታሚ ተፈረደበት /ርዝመት -8ደ35ሰ/
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:36 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የዳዲሞስ ኢንተርቴይንመንት እና የፕሬስ ሥራዎች ድርጅትና በሥራ አስኪያጁ በግዛው ታየ ላይ የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የገንዘብና የእሥራት ፍርድ ሰጥቷል፡፡

ፍርዱ በሌለበት የተላለፈበት ግዛው ታየ በበኩሉ ሲጀመርም ሆን ተብሎ የሕትመት ውጤቶቹን ለመዝጋት ታስቦ የነበረና ያለአግባብ የተመሠረተ ክሥ ነበር ብሏል፡፡

የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ስምንተኛ ወንጀል ችሎት በዳዲሞስ የኢንተርቴይንመንት እና የፕሬስ ሥራዎች ድርጅትና በሥራ አስኪያጁ ግዛው ታየ ላይ ፍርዱን ማሳለፉን ፋና ብሮድካስቲንግ የሚባለው ተቋም ዘግቧል፡፡

ድርጅቱም ሆነ ሥራ አስኪያጁ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ ክሡ እስከተመሠረተበት ጊዜ ድረስ ለአምስት ተከታታይ ዓመታት ኦዲስ አለመደረጋቸውን የፌደራል የገቢዎችና ጉምሩክ መ/ቤት አቃቤ ሕግ የከፈተው የክሥ መዝገብ እንደሚናገር ዘገባው ጠቁሟል፡፡

ስለሆነም ድርጅቱም ሆነ ግለሰቡ ታክስ የማጭበርበር ተግባር ላይ እንደነበሩ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የገቢ ግብር መሰወራቸውን፣ በዚህም ለመንግሥት መግባት የነበረበትን ከስምንት ሺህ በላይ ብር ማሣጣታቸውን በክሡ መመልከቱን ሪፖርቱ ይናገራል፡፡

ፍርድ ቤቱ ረቡዕ፤ ጥቅምት 10/2008 ዓ.ም ባስቻለው ችሎት በድርጅቱ ላይ የ200 ሺህ ብር ቅጣት ሲጥል ሥራ አስኪያጁ ግዛው ታየ በ18 ዓመት ፅኑ እሥራትና በ100 ሺህ ብር የገንዘብ ክፍያ እንዲቀጣ የፈረደበት መሆኑን ዘገባው ገልጿል፡፡

ግዛው ታየ
ግዛው ታየ

ፍርዱን መስማቱን ለቪኦኤ የገለፀው ግዛው ታየ ድርጅቱ “እንዲዘጋ እስከተደረገበት ድረስ የሚፈለግበትን ሁሉ ሲፈፅም መቆየቱን ተናግሯል፡፡

ድርጅቱ የተዘጋና የተወረሰም በመሆኑ የተጣለበትን የ200 ሺህ ብር ክፍያ መፈፀም የማይችል መሆኑን ግዛው አመልክቷል፡፡

ግዛው ቀደም ሲልም በአመፅ በማነሳሳትና መሰል የሽብርተኝነት ወንጀሎች ክሥ ተመሥርቶበት በሃምሣ ሺህ ብር ዋስ ከተለቀቀ በኋላ መሰወሩንና የክሥ ሂደቱ ተከሣሾች በሌሉበት እንዲቀጥል ፍርድ ቤት መወሰኑንና ሂደቱ በተከሣሽ በሌለበት ተሰምቶ ፍርዱም በሌለበት መተላለፉ ታውቋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG