በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የብልጽግና ፓርቲ የዐማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሓላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ ተገደሉ


የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባልና የአማራ ክልል ቅ/ጽ/ቤት ኀላፊ አቶ ግርማ የሽጥላ
የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባልና የአማራ ክልል ቅ/ጽ/ቤት ኀላፊ አቶ ግርማ የሽጥላ

በዐማራ ክልል የገዥው ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሓላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ፣ ተወልደው በአደጉበት አካባቢ መገደላቸውን፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፌስ ቡክ ገጻቸው አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ “ነውጠኛ ጽንፈኞች” ያሏቸውን አካላት፣ ለግድያው ተጠያቂ አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የአቶ ግርማን መገደል በአስታወቁበት የፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ፤ “ከእኛ የተለየ ሐሳብ ማሰብ አልነበረበትም ብለው የሚያምኑ ነውጠኛ ጽንፈኞች፣ የፈጸሙት አስነዋሪ እና አሠቃቂ ተግባር ነው፤" ሲሉ ድርጊቱን በአጽንዖት ኮንነዋል።

አያይዘውም፣ “ጽንፈኝነትን በጊዜ ታግለን ካላስወገድነው ወደ መጨራረስ እንደሚወስደን ጉልሕ ማሳያ ነው፤” ብለዋል።

አቶ ግርማ የሺጥላ የዛሬ ሁለት ዓመት የአማራ ክልል የኢንዱስትሪና የኢንቨስትመንት ቢሮ ሓላፊ እጩ ኾነው ሲቀርቡ ለክልሉ ምክር ቤት በተነበበው የሕይወት ታሪካቸው መሰረት፤ የትውልድ ቦታቸው ሰሜን ሸዋ ዞን መሐል ሜዳ ሲኾን 47 ዓመታቸውን ነው።

XS
SM
MD
LG