በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለሟችዋ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ጊንስበርግ ሀውልት እንደሚሰራ ተገለጸ


ሟችዋ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ሩት ቤደር ጊንስበርግ
ሟችዋ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ሩት ቤደር ጊንስበርግ

ቀኝ ዘመም የሆኑ ዳኞች በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የባላይነት ቦታ ሲይዙ በብዙ ጉዳዮች ላይ ተጽእኖ ያሳድራል። ፕረዚዳንት ትራምፕ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረብዋቸው ኒል ጎርሴችና ብሬት ካቫኖ ሌሎቹ በሪፑብሊካውያን ተሽሞው የነበሩትን ዳኞች ለመተካት ችለዋል።

በአሁኑ ወቅት በዳኛ ሩት ጊንስበርግ ሞት ምክንያት የተገኘውን የሊበራል የነበረውን ክፍት ቦታ በወግ አጥባቂ ዳኛ ለመተካት ከቻሉ ትራምፕ በአንድ ትውልድ ውስጥ ማንም ፕረዚዳንት ሊያገኘው ያልቻለውን ስኬት ያገኛሉ ማለት ነው።

የሟችዋ የዩናትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ሩት ቤደር ጊንስበርግ ሃውልት ኒው ዮርክ ከተማ ውስጥ ተወልደው ባደጉበት ብሩክሊን እንደሚሰራ የኒው ዮርክ ክፍለ-ግዛት አስተዳዳሪ አንድሪው ኮሞ ትላንት አስታውቀዋል።

ጊንስበርግ በ 87 አመት እድሜያቸው በጣፍያ ካንሰር በሽታ ምክንያት ያርፉት ባለፈው አርብ መሆኑ ይታወቃል። በህግ ሙያ አፍላቂነታቸውና በሴቶች መብት ታጋይነት የሚታወቁት ዳኛ እአአ በ1993 አም በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሁለተኛ ሴት ዳኛ ሆነው ተሾሙ።

ዲሞክራቱ አስተዳዳሪ ኮሞ ታድያ የጊንስበግ ሀውልት የሚሰራበት ቦታንና ሀውልቱን የሚሰራ ሰው በመምረጥ የሚያስተባብር ኮሚሽን እንደሚመሰርቱ ገልጸዋል።

XS
SM
MD
LG