ኢሕአደግ መንበረ ሥልጣኑን ከተቆጣጠረ ሩብ ምዕት ዓመት ተጠናቅቆ ሃገሪቱ በዚሁ ሥርዓት ውስጥ መጭውን ዘመን ከጀመረች ባለፈው ግንቦት ሃያ አንድ ዓመት አንስታለች፡፡
ያለፉ ዓመታትን ግምገማ ከተለያዩ የፖለቲካው ቤተሰብ አባላት ጋር እያደረግናቸው ባለናቸው ውይይቶች ጀምረናል፡፡
ካለፉት ዓመታት ገፅታዎች ጎልቶ የሚታየው የግንቦት 7 / 1997 ዓ.ም. ምርጫ ሂደት በሃገሪቱ የፖለቲካና የዴሞክራሲ ታሪክ ውስጥ የማይዘነጋ እሴት፣ ተከትሎም ሰፊ ጠባሳ ያኖረ ቀውስ ፈጥሮ እንዳለፈ ይታወሳል፡፡
በቁጭትና በፀፀት የሚያስታውሱት ጥቂት አይደሉም፡፡ የዴሞክራሲ ተማሪዎችና ተለማማጆች ነን፤ ተምረንበታል የሚሉም የዚያኑ ያህል ናቸው፡፡
ለማንኛውም በቀውሱ ውስጥ በተፈጠሩ ግጭቶች ሕይወታቸውን ያጡ ኢትዮጵያዊያንን ለመዘከር በመኢአድ ፅሕፈት ቤት በቅርቡ ተዘጋጅቶ የነበረውን ዝግጅት መነሻ በማድረግ የአዘጋጆቹን ፓርቲዎች የመኢአድን ምክትል ፕሬዚዳንት የአቶ ሙሉጌታ አበበን እና የሰማያዊ ፓርቲን ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋን አነጋግረናል፡፡
በሁለቱ የፖለቲካ መሪዎች ሃሣብ አሁን ያለው ፓርላማም ሆነ መንግሥቱ በእውነተኛ ምርጫ ሥልጣን የያዙና በሕዝብም የተመረጡ አይደሉም፡፡
ለዘላቂ ሰላምና ለመግባባት ይቅር መባባልና ብሔራዊ ዕርቅ እጅግ አስፈላጊ መሆናቸውን ሁለቱም መሪዎች ይናገራሉ፡፡
ሙሉውን ውይይት ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ