የጊቤ ሁለት ኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ተመርቆ በተከፈተ በጥቂት ቀናት ውስጥ በማስተላለፊያ መሥመሩ ላይ ደርሶ በነበረው የአለት ናዳ ምክንያት ሥራው ለአሥራ አንድ ወራት ተቋርጦ መቆየቱ ይታወሣል፡፡
ጥገናው ተጠናቅቆ የኃይል ማመንጫው አገልግሎት መስጠት የጀመረው ዕሁድ ታኅሣስ 17 ቀን 2003 ዓ.ም ነው፡፡
የአደጋውን ምክንያትና የጥገናውንም ሁኔታ ለማጥናት የኮርፖሬሽኑ መሥሪያ ቤትና ሌሎች ስድስት ዓለምአቀፍ ድርጅቶት መሣተፋቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ምሕረት ደበበ ለአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በሰጡት ማብራሪያ ተናግረዋል፡፡
ግቤ ሁለት ማመንጫ ጣቢያ ተጨማሪ 420 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል በማንኛውም ጊዜ ማቅረብ የሚችል መሆኑን ዋና ሥራ አስፈፃሚው አመልክተዋል፡፡
በግቤ ሁለት አገልግሎት ማቋረጥ መንስዔና በጥገናውም ሥራ ላይ ዋና ሥራ አስፈፃሚውን አቶ ምሕረት ደበበን ሰሎሞን አባተ አነጋግሯቸዋል፤
ለዝርዝሩ ቃለምልልሱን ያዳምጡ፡፡