በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የግቤ ሦስት ግንባታ እንዲቆም ተጠየቀ


የግቤ ሦስት ኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ እንዲቆም የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሣይንስና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) አካል የሆነው የዓለም ቅርስ ጥበቃ ኮሚቴ ጠየቀ፡፡

ይህ World Heritage Committee የሚባለው የዩኔስኮ አካል ባሕላዊና አካላዊም እሴትና ትርጉም ያላቸውን አካባቢዎች እየመዘገበ የሚይዝ ተቋም ሲሆን ግዙፉ ግቤ ሦስት ግድብ እየተገነባ ያለበት ኦሞ ወንዝ የሚገባበትን በኢትዮጵያና በኬንያ ድንበር ላይ ያለውን ቱርካና ሐይቅም በዓለም ቅርስነት መዝግቦታል፡፡

የተቋሙ ቃል አቀባይ ነፃ አካል ነው ያሉት የዓለም ቅርስ ጥበቃ ኮሚቴ ቃል አቀባይ አሜላን ሮኒ 21 አባል መንግሥታት ባሉት ተዘዋዋሪ አመራር የሚገዛ እና በ1972 ዓ.ም (እአአ) በተፈረመ ስምምነት መሠረት ውሣኔዎችን የሚካታተልና የሚያስፈፅም አካል ነው፡፡

ኮሚቴው ግቤ ሦስት እንዲቆም የሚጠይቀውን ውሣኔውን እንዲያሣልፍ ካሳሰቡት ጉዳዮች አንዱ ለቱርካና ሐይቅ ዘጠና ከመቶውን ውኃ የሚያበረክተው ኦሞ ወንዝ መሆኑ እንደሆነ፣ እንዲሁም የአፍሪካ ልማት ባንክ በ2010 ዓ.ም ባወጣው የኢትዮጵያ የኦሞ ተፋሰስ በቱርካና ሐይቅ የውኃ መጠን ላይ ያለውን ተፅዕኖ የሚመለከት ጥናታዊ ሪፖርት መሆኑን የውሣኔው ቃል የሠፈረበት ሠነድ ይናገራል፡፡

በዚህም መሠረት የግቤ ሦስት ግንባታ “እንዲሁም በቋፍ ያለውን የቱርካና ሐይቅ የውኃ ተፈጥሮ፣ የውስጥ ሃብቱንና ሕይወታዊ ሥርዓቱን ሊጎዳ ይችላል፤ ለዓለም ያለውን የላቀ ሁለንተናዊ እሴትም ያናጋል” ብሎ ኮሚቴው እንደሚያምን በሠነዱ ላይ እስፍሯል፡፡

በመሆኑም በዓለምአቀፉ የስምምነት ሠነድ አንቀፅ ስድስት መሠረት የኢትዮጵያ መንግሥት የግቤ ሦስት ግንባታን በአስቸኳይ እንዲያቆም የዓለም ቅርስ ጥበቃ ኮሚቴ ጥሪ አስተላልፏል፡፡

ዝርዝሩን ከዘገባው ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG