በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጋና የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጆን ማሃማ ወደ ስልጣን ሊመለሱ ነው


የቀድሞው የጋና ፕሬዚደንት ደጋፊዎች እና የናሽናል ዲሞክራቲክ ኮንግረስ (ኤንዲሲ) ደጋፊዎች አክራ በሚገኘው የፓርቲው ዋና መሥሪያ ቤት አቅራቢያ ደስታቸውን እየገለጽ እአአ ታኅሳስ 8/2024
የቀድሞው የጋና ፕሬዚደንት ደጋፊዎች እና የናሽናል ዲሞክራቲክ ኮንግረስ (ኤንዲሲ) ደጋፊዎች አክራ በሚገኘው የፓርቲው ዋና መሥሪያ ቤት አቅራቢያ ደስታቸውን እየገለጽ እአአ ታኅሳስ 8/2024

በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ጋና በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ፣ በመንግስት የኢኮኖሚ አያያዝ የተማረሩ መራጮች በሰጡት ድምፅ የገዢው ፓርቲ እጩ የነበሩት ምክትል ፕሬዝዳንት ማሃሙዱ ባዉሚያ መሸነፋቸውን ተከትሎ፣ ተፎካካሪያቸው የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጆን ማሃማ ወደ ስልጣን ሊመለሱ ነው።

የምርጫው ውጤት ይፋ ከሆነ በኃላ ባዉሚያ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ ጋናውያን ለውጥ ለማግኘት የወሰኑትን ውሳኔ እንደሚያከብሩ ተናግረዋል። ለአዲሱ ተመራጭ ፕሬዝዳንት ጆን ማሃማም የእንኳን ደስ አልዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።

እ.አ.አ ከ2012 እስከ 2017 ጋናን የመሩት የ65 ዓመቱ ማሃማ በምርጫው ዘመቻ ወቅት፣ ለኢኮኖሚው ቅድሚያ በሚሰጥ መልኩ ሀገሪቱን በተለያዩ ዘርፎች ድጋሚ እንድታንሰራራ እንደሚያደርጉ፣ ሀገሪቱ ከገባችበት የኢኮኖሚ ቀውስ ለመውጣት ምርጫውን ብቸኛ መንገድ አድርገው ለቆጠሩት ወጣቶች ቃል ገብተዋል።

የማሃማ ማሸነፍ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዓለም ዙሪያ በተካሄዱ ምርጫዎች በስልጣን ላይ ካሉ መሪዎች ይልቅ ተቃዋሚዎችን በመምረጥ፣ በዩናይትድ ስቴትስ፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ እና ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ በበርካታ ሀገራት የታየውን አካሄድ የሚያጠናክር መሆኑም ተገልጿል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG