የቀድሞ የጋና ፕሬዝደንት እና የተቃዋሚ መሪው ጃን ማሃማ ባለፈው ቅዳሜ በተደረገው ምርጫ ማሸነፋቸውን የሃገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ዛሬ ሰኞ አስታውቋል። ማሃማ ወደ ሥልጣን የመመለሳቸው ጉዳይ የተደበላለቁ አስተያየቶችን በማስተናገድ ላይ ነው። አንዳንዶች ማሃማት በአዲስ መልክ ለማስተዳደር በመመለሳቸው ደስታቸውን ሲገልጹ፣ ሌሎች ደግሞ የጋናን የኢኮኖሚ ተግዳሮቶች የመፍታት አቅማቸው ላይ ጥያቄ አላቸው።
የቪኦኤው ሰናኑ ቶድ ከአክራ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም