በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጋና ከአበዳሪዎች ጋር የብድር እዳዋን መልሶ ለማዋቀር ተስማማች


የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት(IMF)
የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት(IMF)

ጋና 5.4 ቢሊዮን ዶላር ዕዳዋን በአዲስ መልክ ለማዋቀር ቻይና እና ፈረንሳይን ጨምሮ ከዓለም አቀፍ አበዳሪዎች ጋር የሁለትዮሽ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመች፡፡

የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ከስምምነት የደረሰችው፣ እዳዋን መክፈል እንደማትችል ይፋ ካደረገች ከአንድ አመት ተኩል በኋላ መሆኑን፣ ሁለት የመንግስት ምንጮች ዛሬ ዓርብ ተናግረዋል፡፡

የመግባቢያ ሰነዱ፣ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ.ኤም.ኤፍ)፣ የጋና እዳ በሶስት ዓመት እንዲሸፈን ከመደበው የ3 ቢሊዮን ዶላር መርሃግብር ውስጥ፣ 360 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ እንዲለቀቅ ይፈቅዳል፡፡ ይህ በሚቀጥለው ወር ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ስምምነቱ አንዴ ከተፈረመ በኋላ፣ የፓሪስ የአበዳሪዎች ክለብ አባላት፣ ባላፈው ጥር ወር በደረሱበት ስምምነት መሰረት፣ ቻይና እና ፈረንሳይን ጨምሮ ኦፊሴላዊ አበዳሪዎች እዳውን መልሶ ለማዋቀር መሠረት ይሆናቸዋል፡፡

ጋና ወደ 30 ቢሊዮን ዶላር ከሚደርሰው የውጭ ብድሯ አብዛኛውን መክፈል ባለመቻሏ፣ እዳቸውን መክፈል ካልቻሉ የአፍሪካ ሀገሮች፣ ከዛምቢያ ቀጥሎ ሁለተኛዋ ሀገር ሆናለች፡፡

ወርቅ፣ ኮኮዋ እና ዘይት የመሳሰሉ ምርቶችን ላኪ የሆነችው ጋና እዳዋን መክፈል ያልቻለችው በኮቪድ ወረረሽኝ ወቅት ሲሆን በዘመናት ከደረሰባት ውድቀት ለመውጣት እየታገለች መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ጋና የዋጋ ግሽበቱን እኤአ በታህሳስ 2022 ከነበረበት 54.1 ከመቶ በሚያዝያ 2024 ወደ 25 ከመቶ በማውረድ ኢኮኖሚዋ ማገገም ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ አይ.ኤም.ኤፍ ከገመተው ከ2.3 ከመቶ በላይ በ2.9 ከመቶ አድጓል፡፡

ከዛምቢያ እና ኢትዮጵያ ጋር በመሆን የዓለማችን ሁለተኛዋ ትልቁ የኮኮዋ አምራች የሆነችው ጋና በቡድን 20 የጋራ ማዕቀፍ ውስጥ ዕዳዋን እንደገና ለማዋቀር እየሰራች ነው፡፡ ይሁን እንጂ ግን በብድር እና ኢንቨርስትመትን እጦት የምጣኔ ሀብት እድገቷ አዝጋሚ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG