በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩክሬኑን ቀውስ ተከትሎ ጋና የወጭ ቅነሳ እምርጃዎችን መውሰድ ጀመረች


ፎቶ ፋይል፦ የጋና ፕሬዚዳንት ናኖ አኩፎ አዶ
ፎቶ ፋይል፦ የጋና ፕሬዚዳንት ናኖ አኩፎ አዶ

የጋናው ፕሬዚዳንትና ሚኒስትሮቻቸው የዩክሬንን ጦርነት ተከትሎ በሃገራቸው ላይ የተከሰተውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን ያስከተለውን ቀውስ ለማርገብ በበርካታ የመንግሥትና የአገሪቱ ወጭዎች ላይ የቅነሳ እምርጃዎችን መውሰዳቸውን አስታውቀዋል፡፡

የጋናው ፕሬዚዳንት ናኖ አኩፎ አዶ እና ሚኒስትሮቻቸው ከወሰዷቸው ሌሎች እምጃዎች በተጨማሪ ከሚያገኙት ገቢ 30 ከመቶ መቀነሳቸውን አስታውቀዋል፡፡

ለአገራቸው ህዝብ መግለጫ የሰጡት የገንዘብ ሚኒስትሩ ኬን ኦፎሪም አታም መንግሥት በሚያደርገው የውጭ ቅነሳ 400 ሚሊዮን ዶላር ለማትረፍ ማቀዱን አመልክተዋል፡፡ በቅነሳው ከተካተቱት ወጭዎች የመንግሥት ባለሥልጣናት ወደ ውጭ አገር የሚያደርጓቸው ጒዞዎች መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

በጋናም ሆነ በሌሎች ያደጉም ሆነ ታዳጊ አገሮች ውስጥ ያሉት መንግሥታት ኮቪድ 19 ከተጎዳው የምጣኔ ሀብት ቀውስና እሱንም ተከትሎ ከመጣው የሸቀጦች አቅርቦታ እጥረትና አሁን ደግሞ የዩክሬን ጦርነት ካስተከለው ችግር ለመውጣት ጠንክረው በመስራት መጠመዳቸውን ገልጸዋል፡፡

XS
SM
MD
LG