በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በታይላንድ ዋሻ ውስጥ ከጠፉ ዘጠኝ ቀናት የሆናቸው ታዳጊዎች በህይወት ተገኙ


የታይላንድ የሀገር አስተዳደር ሚኒስትር በአሥራዎቹ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉትን 12 ልጆችና ጎልማሳ አሰልጣኛቸውን ለማተረፍ ባለሥልጣኖች የሚያደርጉትን ጥረት እንዲያፋጥኑ የከባድ ዝናብ አደጋ አስገድዷል ብለዋል።

የታይላንድ የሀገር አስተዳደር ሚኒስትር በአሥራዎቹ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉትን 12 ልጆችና ጎልማሳ አሰልጣኛቸውን ለማተረፍ ባለሥልጣኖች የሚያደርጉትን ጥረት እንዲያፋጥኑ የከባድ ዝናብ አደጋ አስገድዷል ብለዋል። የእግር ኳስ ተጫዋቾቹ ልጆችና አስልጣኛቸው የገቡበት አልታወቀም ከተባለ ዘጠኝ ቀናት በኋላ ዋሻ ውስጥ በህይወት ተገኝተዋል።

ልጆቹ ከ11 እስከ 16 ዓመታት ዕድሜ ክልል ውስጥ ሲሆኑ ታመ ሉንግ በተባሉት ዋሻዎች ነው የተገኙት። በተረጋጋ ሁኔታ እንደተገኙና ፕሮቲን የበዛበት ፈሳሽ ምግብና መድሃኒቶች እንዳቀረበላቸው ተገልጿል።

የመድኅን ሠራተኛ ቡድኖች ልጆቹንና አሰልጣኛቸውን እንዴት ከዋሻዎቹ ማስወጣት እንዳሚቻል እያጠኑ ናቸው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG