በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጀርመን ወግ አጥባቂዎች፣ ከሶሻል ዲሞክራቶች ጋር ሊወያዩ ነው

የጀርመን ወግ አጥባቂዎች፣ ከሶሻል ዲሞክራቶች ጋር ዛሬ ሰኞ የጥምረት ውይይት ሊጀምሩ መሆናቸው ተሰማ። ይህ የሆነውም፣ ማዕከላዊው ግራ ዘመም ፓርቲ ለወራት የዘለቀውን ፖለቲካዊ አጣብቂኝ ካበቃ በኋላ መሆኑም ታውቋል።

የጀርመን ወግ አጥባቂዎች፣ ከሶሻል ዲሞክራቶች ጋር ዛሬ ሰኞ የጥምረት ውይይት ሊጀምሩ መሆናቸው ተሰማ። ይህ የሆነውም፣ ማዕከላዊው ግራ ዘመም ፓርቲ ለወራት የዘለቀውን ፖለቲካዊ አጣብቂኝ ካበቃ በኋላ መሆኑም ታውቋል።

ወግ አጥባቂው የቻንስሌር አንጌላ መርክል አንድነትና የማርቲን ሰሁልትዝ ሶሻል ዲሞክራት፣ በዚህ ሳምንት ውስጥ ኦፊሴላዊ ውይይት ይጀምራሉም ተብሏል።

ይሁንና ወግ አጥባቂዎች፣ እንደ ኢሚግሬሽን በመሳሰሉ ቅድመ ሥምምነቶች ላይ እንደገና እንደ አዲስ ነጥብ ለመደራደር ዝግጁ እንዳልሆኑ አስጠንቅቀዋል።

ቃል አቀባያቸው ጁሊያ ክሎክነር ለአንድ የቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃል፤ መጪው ድርድር የሚያተኩረው ቀደም ብለው በተስማሙባቸው ነጥቦች ላይ እንጂ፣ ከዚህ በፊት ውድቅ በሆኑት ጉዳዮች ላይ እንደማይሆን ተናግረዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG