ጀርመን በዩናይትድ ስቴትስ የተሰሩ ሰላሳ አምስት ኤፍ - 35 ተዋጊ ጀቶችንና አስራ አምስት ዩሮፋይተር ጀቶችን ልትገዛ ማቀዷ የሀገሪቱ ፓርላማ ምንጮች ጠቆሙ። ይህ ዕቅድ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ከፈጸመችው ወረራ ወዲህ የሃገሪቱን የጦር ኃይል አቅም ለማጠናከር የሚወሰድ እርምጃ መሆኑን ነው ምንጮቹ የገለጡት።
በሎክሂድ ማርቲን ኩባኒያ የተሰሩት ኤፍ 35 ጀቶቹ ጀርመን ከበርካታ አሰርት ዓመታት ጀምሮ ያሉዋትን ቶርኔዶ ጀቶች ለመተካት የታሰቡ መሆናቸውን ዘገባዎች የጠቆሙትን የፓርላማው ምንጮች አረጋግጠዋል። ሎክሂድ ሰራሾቹ ጀቶች በዘመናዊነት በዓለም ወደር የሌላቸው ተዋጊ ጄቶች መሆናቸው እና ቀለማቸውም በጠላት ራዳር እንዳይገኙ የሚረዳቸው መሆኑን ዜናው ጨመሮ አውስቷል።
የጀርመን ቻንስለር ኦላፍ ሾልዝ ከባድ የበጀት ዕጥረት ላለበት የሃገሪቱ የጦር ኃይል 112 ቢሊዮን ዶላር እንደሚድቡ ባለፈው ወር ቃል መግባታቸው ይታወሳል።