በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጀርመን የጦር መርከቧን ወደ ቀይ ባሕር ላከች


የጀርመን የባሕር ላይ የጦር መርከብ
የጀርመን የባሕር ላይ የጦር መርከብ

በቀይ ባሕር ላይ በሚመላለሱ የንግድ መርከቦች ላይ በየመን አማጺያን የሚሰነዘረውን ጥቃት ለመከላከል በሚል፣ አንድ የጀርመን የባሕር ላይ የጦር መርከብ ትናንት ወደ አካባቢው መቅዘፍ ጀምሯል። የአውሮፓ ኅብረት ተልዕኮ አካል መሆኑ ተነግሯል።

ውሳኔው ለጀርመኖቹ ባሕር ኃይል ከአስርተ ዓመታት በኋላ የሚደረግ ትልቁ ተልዕኮምነው ተብሏል።

የእስራኤልና የሐማስ ጦርነት መፈንዳትን ተከትሎ፣ በየመን የሚገኙት እና በኢራን ይደገፋሉ የሚባሉት የሁቲ አማጽያን ካለፈው ህዳር ጀምሮ በቀይ ባሕር ላይ በሚመላለሱ መርከቦች ላይ ጥቃት ሲሰነዝሩ ቆይተዋል። ከፍልስጤማውያን ጋር ያላቸውን አጋርነት ለማሳየት የሚፈጽሙት ጥቃት እንደሆነ አማጺያኑ ይገልጻሉ።

በቀይ ባሕር ላይ 12 በመቶ የሚሆነው የዓለም የንግድ መርከቦች እንቅስቃሴ የሚካሂድበት ሲሆን፣ የሁቲዎችን ጥቃት ተከትሎ መርከቦች በአፍሪካ ደቡባዊ ጫፍ በኩል እንዲዞሩ ተገደው ነበር። የመርከቦቹን ወጪም ሆነ የሸቀጦችን ዋጋ እንዲጨምር አድርጓል ተብሏል።

የጀርመኑ የጦር መርከብ ከሁቲዎች ለሚሰነዘረው የሚሳዬል እና የድሮን ጥቃት ምላሽ እንደሚሰጥ እና የንግድ መርከቦችንም እንደሚያጅብ ይጠበቃል።

የጣሊያን፣ የፈረንሣይ እና የቤልጂየም መንግስታትም ተልዕኮውን ለመቀላቀል እንደሚሹ ማስታወቃቸውን የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።

የአሜሪካ እና የእንግሊዝ ኃይሎች ቀደም ሲል ጀምሮም የሁቲ አማጺያንን አቅም ለማሳሳት ተደጋጋሚ ድብደባ ሲያደርጉ ቆይተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG