ለዩክሬን የምትሰጠውን ድጋፍ እንድታቆም ለማስገደድ ሩሲያ ለምትሰነዘረው ዛቻ እንደማትንበረከክ ጀርመን አስታውቃለች፡፡
ሩሲያ አንድ ከፍተኛ የጀርመን መሣሪያ አምራች ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚን ለመግደል ማቀዷን የአሜሪካ ደህንነት ደርሶበታል ሲል ሲኤንኤን አምስት የአሜሪካ እና የምዕራባዊ ሃገራትን ባለሥልጣናትን ጠቅሶ ትላንት ሐሙስ ዘግቦ ነበር። ጀርመን በዘገባው ላይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥባለች፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ አሜሪካ ጉዳዩን ለጀርመን አስታውቃ የሃገሪቱ የደህንነት ኃይል የግድያ ዕቅዱን እንዳከሸፈ ተውቋል። ግድያ ሊፈጸምባቸው የነበሩትም ራይንሜታል የተሰኘው የተሽከርካሪና የመሣሪያ አምራች የሆነው ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አርሚን ፓፐርጀር እንደሆኑ ታውቋል።
የጀርመን የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዛሬ ዓርብ እንዳሉት ከሩሲያ በኩል እየጨመረ የመጣውን ዛቻ እና ጠብ ጫሪነት ተገቢውን ትኩረት እንደምሰጠው አስታውቀዋል።
ሩሲያ የሲኤንኤንን ዘገባ ውድቅ አድርጋለች፡፡
መድረክ / ፎረም