በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጀርመን ፍልሰኞች በመኪና አደጋ ሞቱ


ሙኒክ፣ ጀርመን
ሙኒክ፣ ጀርመን

ጀርመን ውስጥ ሰዎችን በህገ ወጥ መንገድ ያስተላልፍ በነበረ ሰው ይሾፈር እንደነበር የተጠረጠረ መኪና ፖሊስ እንዳያስቆመው ለማምለጥ ሲሞክር ተገልብጦ ተሳፍረውበት የነበሩ ሰባት ሰዎች መሞታቸውንና ሌሎች ደግሞ መቁሰላቸውን ባለሥልጣናቱ አስታወቁ።

ከሙኒክ ከተማ ወደ ምሥራቅ የሚወስደውና አደጋው የደረሰበት ኤ94 የሚባለው አውራ ጎዳና ሰዎችን በህገወጥ በማስተላለፊያ መሥመርነቱ ቀድሞም የሚታወቅ ሲሆን አሸከርካሪው ዛሬ መኪናውን መቆጣጠር ያቃተው ወደ ኦስትሪያ ድንበር እየነዳ ሳለ እንደነበር ተነግሯል።

በተሽከርካሪው ሚኒቫን ውስጥ ህፃናትን ጨምሮ የሶሪያና የቱርክ ዜጎች የሆኑ ከሃያ በላይ ተሣፋሪዎች እንደነበሩ ተገልጿል።

አሽከርካሪው የማንም ሃገር ዜግነት የሌለው መሆኑን አሶሲየትድ ፕሬስ ዘግቧል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወደ አውሮፓ የሚገባው ፍልሰተኛ ቁጥር እየጨመረ መምጣቱና ለብዙዎቹ ፍልስተኞች ጀርመን ዋና መዳራሻቸው መሆኗ በዘገባው ተጠቅሷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG