የጀርመን ካቢኔ በካናቢስ ላይ የተጣለውን ሕግ ላላ ለማድረግ ውሳኔ እንደሚሰጥ በመጠበቅ ላይ ነው። ይህም የአውሮፓ ሕብረት በተወሰነ መጠን ካናቢስን ይዞ መገኘት እንዳያስከሥስ እንዲያደርግ ጥርጊያ መንገድ ይከፍታል ተብሏል። ተጠቃሚዎችም ለመዝናናት ያህል የሚበቃቸውን መግዛት እንዲችሉ ያስችላል ተብሏል።
ዛሬ በካቢኔ ይጸድቃል ተብሎ የሚጠበቀው ደንብ፣ በፓርላማው መጽደቅ ይጠበቅበታል።
የቀኝ ክንፍ ተቃዋሚው፣ በአውሮፓ የህግ እንቅፋቶች እያሉም፣ መንግስት አደገኛ ሕጽን ህጋዊ ለማድረግ እየሞከረ ነው ሲሉ ይከሳሉ።
ይወጣል በተባለው ደንብ መሠረት ሰዎች እስከ 25 ግራም ካናቢስ ለመዝናኛ ጠቀሜታ መያዝ ሲችሉ፣ ሶስት እግር ተክልም ቤታቸው ማሳደግ ይችላሉ።
ዕቅዱ የጥቁር ገበያን የሚያስወግድ እና የተበከሉ ምርቶች ለገበያ እንዳይቀርቡ እንዲሁም በአደንዛዥ እጽ ምክንያት የሚመጡ ወንጀሎችን ይቀንሳል ሲሉ ባለሥልጣናት ይናገራሉ።
መድረክ / ፎረም