ጀርመን ወታደራዊ መረጃዎችን ለቻይና ሰጥቷል በሚል የተጠረጠረውን የአሜሪካ ዜጋ በቁጥጥር ስር አዋለች።
ጀርመን በሀገሯ ለሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሲሰራ ያገኘውን የአሜሪካ ወታደራዊ መረጃ ለቻይና በመስጠት የተጠረጠረውን የአሜሪካ ዜጋ በቁጥጥር ስር ማዋሏን፣ የሀገሪቱ ፌደራል አቃቤ ህግ ፅህፈት ቤት ዛሬ ሃሙስ ዕለት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
መግለጫ እንዳመልከተው የግል ማንነትን አለመግለጽ በሚፈቅደው የጀርመን ህግ መሰረት ማርቲን ዲ በሚል ስም ብቻ የተገለጸው ግለሰብ ለውጭ የስለላ ድርጅት ወኪል ሆኖ ለመስራት መዘጋጀቱን ተናግሯል ሲል አመልክቷል፡፡
ተከሳሹ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በጀርመን ለአሜሪካ ጦር ሃይሎች ሲሰራ እንደነበር አቃቤ ህግ ተናግሯል።
እ.ኤ.አ. በ2024 ከቻይና የመንግስት ባለስልጣናት ጋር በመገናኘት ለቻይና ጥብቅ መረጃዎችን እንደሚያካፍላቸው ተነግሯል። መረጃውን የሰበሰበው ለውትድርና ባደረገው ስራ ነው ሲል አቃቤ ህግ ተናግሯል።
ጀርመን ከቤጂንግ የሚዘረጉ የስለላ መረቦች ሊጨምሩ እንደሚችሉ ያላትን ስጋት በመግለጽ ያስጠነቀቀች ሲሆን በዚህ ዓመት በስለላ ተግባር የተጠረጠሩ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሏን አስታውቃለች፡፡
ይህ በሚያዝያ ወር ላይ የቻይናን የባህር ሃይል የሚያጠናክር ቴክኖሎጂን አሳልፈው ለመስጠት ሲሰሩ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ሶስት ጀርመናውያን እና ከቻይና የስለላ ድርጅት ጋር በመስራት የተከሰሱትን የቀኝ አክራሪ ፖለቲከኛ የአውሮፓ ህብረት ሰራተኛን ያጠቃልላል።
መድረክ / ፎረም