በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጀርመን በሙኒክ ኦሎምፒክ ለተገደሉት አትሌቶች 28 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ትከፍላለች


እአአ በ1972 በተካሄደው የሙኒክ ኦሎምፒክ ለተገደሉ የእስራኤል አትሌቶች የተቀመጠው የመታሰቢያ ድንጋይ
እአአ በ1972 በተካሄደው የሙኒክ ኦሎምፒክ ለተገደሉ የእስራኤል አትሌቶች የተቀመጠው የመታሰቢያ ድንጋይ

ጀርመን እአአ በ1972 በተካሄደው የሙኒክ ኦሎምፒክ ለተገደሉ የእስራኤል አትሌቶች ቤተሰቦች 28 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ለመክፈል መስማማቷን የጀርመንን የአገር ውስጥ ሚኒስቴር ቃል አቀባይን ጠቅሶ ሮይተር ዛሬ ዘግቧል፡፡

እአአ መስከረም 5/1972 የእስራኤል ኦሎምፒክ ቡድን አባላት የሆኑት ታጋቾች፣ ደህንነቱ በሚገባ ካልተጠበቀ የኦሎምፒኩ መንደር በፍልስጤማውያንና፣ ብላክ ስፕቴምበር ግሩፕ በተባለው ቡድን አባላት ታግተው መወሰዳቸው ይታወሳል፡፡

በወቅቱ 24 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥም ታጋቾቹን ለማስለቀቅ በተደረገ የተኩስ ልውውጥ 11 እስራኤላውያን አትሌቶች፣ አምስት ፍልስጤማውያንና አንድ የጀርመን ፖሊስ መገደላቸው ተዘግቧል፡፡

XS
SM
MD
LG