በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጀርመን ፖሊስ የሐማስ አባላትንና ደጋፊዎችን ንብረት ፈተሸ


በመቶ የሚቆጠሩ የጀርመን ፖሊሶች፣ የሐማስ አባላት እና ደጋፊዎች ናቸው ያሏቸውን ሰዎች ንብረት ፈትሸዋል። ፍተሻው በተለይም፣ በበርሊን ከተማ ጠንከር ያለ እንደነበር፣ አሶሽየትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል።

የጀርመን መንግሥት፣ በሐማስም ኾነ በደጋፊዎቹ የሚካሔድን ማንኛውንም እንቅስቃሴ፣ ከሦስት ሳምንት በፊት አግዶ ነበር። በተጨማሪም፣ “ሳሚዱን” የተሰኘና ሐማስ በእስራኤል ላይ ጥቃት የከፈተበት ቀን እንዲከበር ያዘጋጀውን ቡድን አግዷል።

ሐማስንና ሳሚዱንን ማገዳችን፥ ሐማስ የሚፈጽመውን ድርጊት ማወደስ፣ በጀርመን ተቀባይነት እንደሌለው ግልጽ መልዕክት ያስተላልፋል፤”

“ሐማስንና ሳሚዱንን ማገዳችን፥ ሐማስ የሚፈጽመውን ድርጊት ማወደስ፣ በጀርመን ተቀባይነት እንደሌለው ግልጽ መልዕክት ያስተላልፋል፤” ሲሉ፣ የአገር ውስጥ ሚኒስትር ናንሲ ፌሰር ተናግረዋል።

ከፍተሻው በላይም፣ በቡድኖቹ ላይ ምርመራ እንደሚደረግ፣ የአገር ውስጥ ሚኒስቴር መ/ቤቱ አስታውቋል።

የጀርመን የአገር ውስጥ የደኅንነት ቢሮ እንደሚገምተው፣ በአገሪቱ፣ 450 የሚደርሱ የሐማስ አባላት ይገኛሉ። እኒኽም፣ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በማድረግና በልዩ ልዩ መንገዶች ለሐማስ ድጋፋችውን በመግለጽ እንደሚሳተፉ፣ አሶሽየትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG