በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዳያስፖራው አስተያየት በትረምፕ ንግግር ላይ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ባለፈው ዓርብ፣ የታላቁን ህዳሴ ግድብ አሰመልከቶ “ግብፅ ግድቡን ልታፈነዳው ትችላለች” በሚል ያሰሙንት ንግግር በበርካታ ኢትዮጵያውያን መካክል ቁጣን የቀሰቀሰና አነጋገሪ ሆኖ ሰንብቷል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥትም የትረምፕ ንግግር “ኃላፊነት የጎደለው” መሆኑን ጠቅሶ “ኢትዮጵያ በየትኛውም ማስፈራሪያና ጫና የማትንበረከክ መሆኑን” በጠቅላይ ሚኒስትርና በተወካዮች ም/ቤት በኩል ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ተቀማጭነታቸው በኢትዮጵያ የሆነውን የአሜሪካ አምባሳደርንም በመጥራት ስለ ፕሬዚዳንቱ ንግግር ምንነት መግለጫ እንዲሰጡ ጠይቋል፡፡

በውጭ አገር የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውንም አስተያታቸውን በተለያይ መልኩ እየገለጹ ሲሆን የአሜሪካ ድምፅ አንዳንዶቹን አነጋግሯል፡፡

የኢትዮጵያ ውሃ ጉዳዮች ምክር ቤት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ኮነ ፍሰሃ እና በአባይ ግድብ ላይ በሪፐብሊካንና የዴሞክራቲክ ፓርቲ አባላት በሆኑት የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ሥራ አስፈጻሚ አባላት ላይ መራጮች ደብዳቤዎችን በመላክ ተጽእኖ እንዲያደርጉ ግፊት ለማድረግ ከወራት በፊት የተቋቋመው የመራጮች ድምጽ /ቮተርስ ቮይስን/ አስተባባሪ አቶ ታዳኤል እምሩን አነጋገረናል፡፡

በውጭ ሃገር የሚኖሩ ሌሎች ዕውቅ የፖለቲካ ሰዎች በተለያዩ መድረኮች የሰነዘሯቸውንና የግብጽ መገናኛ ብዙሃን ጉዳዩን አስመልከቶ የሰጡትን መግለጫዎች ይዘናል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡

የዳያስፖራው አስተያየት በትረምፕ ንግግር ላይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:23 0:00


XS
SM
MD
LG