አዲስ አበባ —
ተቋርጦ የነበረው የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና የግብፅ የኅዳሴ ግድብ ድርድር ሰሞኑን አንሠራርቶ የውኃ ሚኒስትሮቹ ሲነጋገሩበት ስንብተዋል።
ቴክኒካዊ በሆኑ ጉዳዮች መግባባት ላይ የተደረሰ ቢመስልም ስምምነቶቹን በሕግ ማዕቀፍ ለማሰር የሚያስችል መግባባት ግን ገና እንደሌለ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ለመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ሰሞኑን ተናግረዋል።
ድርድሩ እንደገና ሊጀመር ፍንጭ መታየቱን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂዖፖሊቲክስና የአፍሪካ ጥናት መምህርና ተመራማሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ታፈሰ በመገናኛ ብዙኃን ያወጡትን ፅሁፍ በመንተራስ ቪኦኤ አነጋግሯቸዋል። የመጀመሪያው ክፍል ቀደም ሲል ተደምጧል።
መለስካቸው አምሃ ለፕሮፌሰር ተስፋዬ ካቀረበላቸው ጥያቄዎች አንዱ፤ “ይህ ድርድር ከታላቁ ኅዳሴ ግድብ ምኅዋር እንዳይወጣ ይፈራሉ፤ ድርድሩ በዚህ ዙሪያ ብቻ እንዲያተኩርና እንዲያበቃ ነው የሚፈልጉት፤ ለምን? የሚል ነበር - ፕሮፌሰር ተስፋዬ ታፈሰ ይመልሳሉ።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።