በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለባይደን አስተዳደር ወሳኝ የሆነው ምርጫ ዛሬ በጆርጂያ ይካሄዳል


በዩናይትድ ስቴትስ ደቡባዊ ክፍለ ግዛት በጆርጂያ የሚገኙ መራጮች
በዩናይትድ ስቴትስ ደቡባዊ ክፍለ ግዛት በጆርጂያ የሚገኙ መራጮች

በዩናይትድ ስቴትስ ደቡባዊ ክፍለ ግዛት በጆርጂያ የሚገኙ መራጮች ዛሬ ማክሰኞ ወደ ድምጽ መስጫው ስፍራዎች ሲያመሩ ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት በአሜሪካ የሚኖረውን የኃይል ሚዛን በመወሰን ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታሉ፡፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ትላንት ሰኞ በጆርጂያ የምርጫ ቅስቀሳ ላይ ነበሩ፡፡ አሁንም እንደተለመደው ስለምርጫው መጭበርበር አንስተዋል፡፡

“ጆርጅያ ላይ ልንሸነፍ የምንችልበት ምንም መንገድ የለም፡፡ የተጭበረበረ ምርጫ ነው፡፡”

ትራምፕ ይህን የሚሉት፣ መራጮች ወደ ድምጽ መስጫ ሄደው፣ ምክር ቤቱን ለመቆጣጠር፣ በድጋሚ የሚወዳደሩትን፣ ሪፐብላኪን እንደራሴዎች፣ ሴነተር ኬሊ ሎዌፍለር እና ዴቪድ ፕሩድን መምረጥ ያለባቸው መሆኑን እያሳሰቡ ነው፡፡ በጆርጂያ የትራምፕ ደጋፊ ላማር ከትስ፣ እንዲህ ይላሉ

“ድምጼን የሰጠሁት፣ ባለፈው ምርጫ ወቅት የተደረገው ነገር የፈጠረብኝ ጥርጣሬ አሁንም እንዳለ ሆኖ መሆኑን አልክድም፡፡”

ለፕሬዚዳንቱ ደጋፊዎች፣ በምርጫው መጭበርበር ካላቸው እምነት በላይ፣ ዴሞክራቶቹን ተፎካካሪዎች፣ ጆን ኦሶፍ እና ራፋኤል ዋርናክን ማሸነፍ በጣም ወሳኝ ነገር ሆኗል፡፡ የፕሬዚዳንቱ ደጋፊ ማርክ ሄስ ፣ እንዲህ ብለዋል

“ሥልጣኑን ይወስዱታል፡፡ የተወካዮቹንም የእንደራሴዎችንም ምክር ቤት፡፡ ያ በታክስ ከፋዮች ላይ የሚኖራቸው ትልቁ ሥልጣን ይሆናል፡፡ ታክሳችን በጣም ይጨምራል፡፡ ጠመንጃዎቻችንን ሊወስድቡን ይሞክራሉ፤ ያ ግን በጣም መጥፎ ይሆናል፡፡ ዴሞክራቶች መሄድ በሚፈልጉበት መንገድ የሚሄዱ ከሆነ፣ ያ በጣም ያስፈራኛል፤ ውጤቱ እጅግ መጥፎ ሊሆን ይችላል፡፡”

በአትላንታ ዙሪያ ያሉት መራጮች፣ ድጋፋቸውን ከሪፐብሊካን ወደ ዴሞክራቶች እንዲዞር በማድረጋቸው፣ ተመራጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ የጆርጅያን ግዛት ከ12ሺ ባነሰ ድምጽ አሸነፈዋል፡፡ እንዲህ ብለዋል ባይደን

“ጆን እና ረቨርንድን በመምረጥ ለአገሪቱ ጠንከር ያለ መልዕክት ማስተላለፍ ትችላላችሁ”

በጣም ጠባብ በሆነ ልዩነት፣ በሚወዳደሩበትና፣ በተለምዶ የሪፐብሊካኖች አካባቢ በሆነው ጆርጂያ፣ ዴሞክራቶች ለማሸነፍ ትልቅ አቀበት እንደመወጣት ይሆንባቸዋል፡፡ ደጋፊዎቻቸውን አንቃንቀው፣ ሁለቱን የእንደራሴ ምክር ቤት መቀመጫዎች ለማሸነፍ፣ ትልቅ ጥረት ይጠይቃል፡፡ የዴሞክራቶቹ እጩ እንደራሴዎች ምርጫ ዘመቻ፣ የበጎ ፈቃድ አስተባባሪ የሆኑት፣ ኬራ ኦልየን እና ሽዋን ዋትኪንስ፣ ወጣቶችንና የተለያዩ የማህበረሰብ አባላትን ይቀስቃስሉ፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ፣ ክፍለ ግዛቲቱን በመለወጥ፤ እነዚህ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ፡፡ ሽዋን ዋትኪንስ እንዲህ ይላሉ

“እንደ እውነቱ ከሆነ እስከዛሬ ሁለት ዓመት ድረስ ፖለቲካ ውስጥ ብዙም እምሳተፍ አልነበርኩም፣ ይሁን እንጂ ግን ከትራምፕ ጋር እየተካሄደ ያለው ነገርና አገሪቱም የገባችበት ሁኔታ፣ ወደ አደባባይ ወጥቼ አሁን እማደርገውን ዓይነት ነገር እንዳደርግ ገፋፍቶኛል፣ ሰዎችም እንደኔው ወጥተው ነገሮችን ወደ ጥሩ ነገር እንደሚለውጣቸው በትክክል አምናለሁ”

የዴሞክራቶቹ ደጋፊ ኬራ ኦልየን፣ ትራምፕ በጆርጂያ የደረሰባቸውን ሽንፈት ይጠራጠራሉ እንጂ፣ የጆርጂያ ማህበረሰብ ስብጥር፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየተቀየረ መመጣቱን አይቀበሉም ይላሉ፡፡

“እንደኔ አስተያየት ከሆነ ይሄ ትክክለኛ የትራምፕ ጠባይ ነው፡፡ በርግጥ የምርጫውን ውጤት በቀላሉ ይቀበላሉ ብዬ አልጠብቅም፡፡ እንደሚመስለኝ ከሆነ ሁል ጊዜም የሪፐብሊካን ግዛት ሆና የቆየቸው ጆርጂያ ወዲያው ብድግ ብላ ድንገት ስትለወጥ “አሃ የተጭበረበረ አለ ማለት ነው” የተባለ ይመስለኛል፡፡ምንም ይሁንም ምን ለውጥ ግን ሁሌም ሊኖር የሚችል ነገር ነው፡፡ በትክክል የተፈጠረውም ነገር ያ ይመስለኛል፡፡”

ከእስከዛሬዎቹ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው መራጮች፣ ወደ ጆርጅያ ምርጫ ጣቢያዎች መሄድ የጀመሩት አስቀድመው ነው፡፡ ዴሞክራቶቹ ሁለቱንም መቀመጫዎች የሚያሸነፉ ከሆነ፣ ሁለቱም ፓርቲዎች በምክር ቤቱ እኩል ድምጽ ይኖራቸዋል፡፡ ያ በሆነ ጊዜ፣ ተመራጯ ምክትል ፕሬዚዳንት ከማላ ኻሪስ፣ የሳቸውን ተጨማሪ ድምጽ በመስጠት፣ አብላጫውን ይወስናሉ፡፡ ይሁን እንጂ፣ ብርቱ ፉክክር ከተያበት የጆርጅያው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በኋላ፣ የፕሬዚዳንቱ ደጋፊዎች ውጤቱን በጸጋ እንደማይቀበሉ ገልጸዋል፡፡ የፕሬዚዳንቱ ደጋፊ ማርሌና ሃርፐር

“በፕሬዚዳንታዊው ምርጫ የተጭበረበረ ነገር ኖሮ ከሆነ እንደዚያው እንደተጭበረበሩ እንዲቀሩ አልተዋቸውም፡፡” ብለዋል፡፡

ይህ ሁኔታ መኖሩ፣ የምርጫው ውጤት የሚገለጽበት ቀን፣ ምናልባት፣ የዛሬው ማክሰኞ ቀን ላይሆን የሚችልበት ሁኔታን፣ ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋት አሳድሯል፡፡ ዘገባው በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የቪኦኤ ዘጋቢ የካትሪን ጊብሰን ነው፡፡

ዝርዙርን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ለባይደን አስተዳደር ወሳኝ የሆነው ምርጫ ዛሬ በጆርጂያ ይካሄዳል
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:51 0:00


XS
SM
MD
LG