በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደሪክ ሻውቪን ላይ የተበየነው የግድያ ወንጀልና የዓለም ምላሽ


ጆርጅ ፍሎየድ
ጆርጅ ፍሎየድ

የ46 ዓመት ዕድሜው አፍሪካዊ አሜሪካዊ ጆርጅ ፍሎየድ ሚኒያፖሊስ ላይ በፖሊስ መገደል በዓለም ዙርያ

"የጥቁሮች ህይወትም ዋጋ አለው” በሚል መሪ ቃል ተቃውሞ ማስነሳቱ የሚታወቅ ነው። የአሜሪካ ድምፅ ዘጋቢ ሄንሪ ሪጅዌል በዘገበው መሰረት ትናንት በደሪክ ሻውቪን ላይ የተሰጠው የግድያ ብይን በብዙ ሀገሮች መልካም ምላሽ አግኝቷል። ሆኖም ገና ብዙ መሰራት ያለባቸው ነገሮች አሉ ሲሉ ለእኩልነት የቆሙ አክትፊስቶች ማሳሰባቸው አልቅረም።

ጆርጅ ፍሎይድን የገደለው የቀድሞ ፖሊስ ደሪክ ሻውቪን፣ ጥፋተኛ ሆኖ መገኝቱ እንደተሰማ፣ ሚኒያፖሊስ ላይ በቦታው ተሰባስበው የነበሩት ሰዎች በከፍተኛ ስሜትና በመልካም መንፈስ ተቀብለውታል። በዓለም ዙርያ የተከታተሉት በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ስዎችም እንደዚሁ።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሸል ባችሌት ሃስባቸውን ገልጸዋል።

ዝርዝሩን ከተያይዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ

በደሪክ ሻውቪን ላይ የተበየነው የግድያ ወንጀልና የዓለም ምላሽ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:49 0:00


XS
SM
MD
LG