በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የገነት ምትኬ አስከሬን አረፈ


ጋዜጠኛ ገነት ምትኬ
ጋዜጠኛ ገነት ምትኬ

የጋዜጠኛ ገነት ምትኬ አስከሬን ሥርዓተ ቀብር ትናንት፤ ዕሁድ፤ ጥር 1/2014 ዓ.ም. አዲስ አበባ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከናውኗል።

በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን፣ ለተወሰኑ ዓመታት ደግሞ በአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ የአማርኛ ዝግጅት ክፍል በጋዜጠኛነት፣ እንዲሁም በአፍሪካ ዲቪዥን ውስጥ በፕሮድዩሰርነት ያገለገለችው ወ/ሮ ገነት ያረፈችው በ65 ዓመት ዕድሜዋ ትኖርበት በነበረው ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ነው።

ወ/ሮ ገነት በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ሥር በሚሰጡ የወጣት ዲፕሎማቶች የቋንቋ ክህሎት ማበልፀጊያ መርኃግብር ላይም ተሣትፋ አማርኛ አስተምራለች፤ ብዙዎችንም አስችላለች።

ገነት ምትኬ በተጨማሪም ኢትዮጵያ ውስጥ ጎጂ ባህላዊ ልማዶችን ለማስወገድ ይደረግ በነበረ ጥረት ውስጥ በንቃት የተሳተፈች ከመሆኑም በተጨማሪ ዩናይትድ ስቴት ውስጥ በሚገኘው “ድሪም ኢትዮጵያን ኮንሶርቲየም” በሚባል የአረጋዊያን ማኅበር ውስጥ በበጎ ፈቃደኝነት አገልግላለች።

የሁለት ወንድ ልጆች እናት የነበረችው ጋዜጠኛ ገነት ምትኬ በሕይወቷ የመጨረሻ ዓመታት ለሕፃናት የሚሆኑ መፅሓፍትን በማዘጋጀት ላይ እንደነበረችም ታሪኳ ያስረዳል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የገነት ምትኬ አስከሬን አረፈ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:44 0:00


XS
SM
MD
LG